የኢትዮጵያ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከውሃ፣ መስኖና የኢነርጂ ሚኒስቴር “ከአካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን እና ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም (UNDP) ጋር በመተባበር ከ GEF በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ" ለቤት ውስጥ ፍጆታና ለማምረቻ አገልግሎት የሚሆን ቀጣይነት ያለው የገጠር ኢነርጂ ቴክኖሎጂ ማበረታቻ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ ተግባረዊ ለማድረግ በገጠር ኢነርጂ ዘርፍ ለተሰማሩ ኢንተርፕራይዞችና የፈጠራ ስራ በላቤቶች በፀሀይ የገጠር ኢነርጂ ቴክኖሎጂ፣ በነዳጅ የገጠር ኢነርጂ፣በንፋስ ሀይል የገጠር ኢነርጂ፣በባዮጋዝ የገጠር ኢነርጂ እና በሌሎች የገጠር ኢነርጂ ዘርፍ ከመጋቢት 04 ቀን ጀምሮ እስከ መጋቢት 25 ቀን 2012 ዓ.ም አመልካቾች እንዲወዳደሩ መጋበዙ ይታወሳል፡፡

ነገር ግን ወቅታዊው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት አሳሳቢ እየሆነ በመምጣቱ ምክንያት በተለያዩ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በአካል በመንቀሳቀስ ተወዳዳሪዎችን ለመመዝገብና እጩዎችን መመልመል አልተቻለም፡፡ በዚህም ምክንያት ለመወዳደር የተመዘገቡ አመልካቾች ቁጥር እጅግ በጣም አነስተኛ ሆኗል፡፡ ስለሆነም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይህንን ጉዳይ ከግምት ውስጥ በማስገባት አመልካቾች ስራዎቻቸውን በቀጥታ /online /ወይም በኢ.ሜይል ማቅረብ እንዲችሉ ስርዓቶችን ዘርግቷል::

ስለሆነም ለውድድድር የማመልከቻ ጊዜን በማራዘም አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 20 ቀን 2012 . ማመልከት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ተወዳዳሪዎችም ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ድረ ገፅ  WWW.MINT.gov.et/competition call ፎርሙን በማውረድ ወደ atirenegash@gmail.com በመላክ ወይም በቀጥታ/ online/ በ https://forms.gle/v4YyLqhtMZD2xHwN9 በመመዝገብ መወዳደር  ይችላሉ፡፡

በለጠ መረጃ በድረ ገፃችን WWW.MINT.gov.et  ወይም በፌስቡክ አድራሻችን Ministry of Innovation and Technology - Ethiopia ማግኘት ይችላሉ፡፡ አልያም በስልክ ቁጥር 0911661675 ወይም 0912612679 ይደውሉ፡፡

          የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር