+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ሁሉን ያሳተፈ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ስነምህዳር አካቶ ትግበራ ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሁሉን ያሳተፈ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን የአካቶ ትግበራ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል ።

የግንዛቤ ማስጨበጫመድረኩ አካቶ ትግበራን በመጠቀም ፆታና ስርዓተ ፆታ፣ ህፃናት፣ ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያን እና ሌሎች ተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎችን በሳይንስና በቴክኖሎጂ ዘርፉ እኩል የኢኮኖሚ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ ነው።

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ኤልሳቤጥ ገብረስላሴ በሀገራችን ሁሉን ያሳተፈ የሳይንስና ቴክኖሎጂ አካቶ ትግበራ ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል የሚሳተፍበት የቴክኖሎጂ አውድ መፍጠር ለሀገር እድገት መሰረት ነው ያሉት ስራ አስፈፃሚዋ በሀገራችን በቴክኖሎጂው ዘርፍ እየተገነቡ ባሉ ምቹ ስነምህዳሮች ላይ እኩል ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ አካቶ ትግበራ ሚናው የላቀ ነው ብለዋል።

የቴክኖሎጂው ዓለም ከአድሎአዊ አስራር የፀዳ ስለሆነ ሁሉም የራሱን አቅም በተገኘው አጋጣሚ በማጎልበት ሊጠቀምበት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

አካቶ ትግበራን ወደ መሬት ለማውረድ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ለዘርፉ ተዋናይ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ማህበረሰብ ላይ በትኩረት መሰራት እንዳለበት ተሳታፊዎች አንስተዋል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ