+251118132191
contact@mint.gov.et
የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ውድድሮች ጎልብተው ወደ ውጤት ሊቀየሩ እንደሚገባ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ገለፁ ።
በአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለሶስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 10ኛው ብሔራዊ ዓመታዊ የሳይንስ እና ኢንጂነሪንግ አውደ ርዕይ ለአሸናፊዎች ልዩ እውቅና እና ሽልማቶችን በመስጠት ተጠናቋል።
በመዝጊያ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ በሀገራችን የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ ለማጎልበት የብሔራዊ የሳይንስና ኢንጂነሪንግ አውደ ርዕይና ውድድሮች ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳላቸው አስገንዝበዋል።
የምንፈልገው ለውጥ ለማምጣት የቴክኖሎጂና የፈጠራ አቅማችን በውድድር ሊጎለብት ይገባል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው እያስተዋልናቸው ያሉት ፈጠራዎች ነገ ከሀገራችን አልፈው አለምን የመቀየር አቅም ያላቸው መሆናቸውን ጠቁመዋል።
መንግስት የኢኖቬሽን ስነምህዳር ለመገንባት በሰው ሀይል ልማት፣ በመሰረተ ልማትና በህግ ማዕቀፍ ላይ ሰፋፊ ስራዎችን በመስራት የወጣቱን ኃይል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተጋ መሆኑን አንስተዋል።
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ ያደጉና ያላደጉ ሀገርች የልዩነታቸው መነሻ የሆነው በቴክኖሎጂና በፈጠራ ላይ የሰጡት ትኩረት መሆኑን ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ የስቲምፓዎር(STEMpower) ኃላፊ ዶ/ር ስመኔው ቀስቅስ የወጣት ፈጣሪዎች ስኬት ከሽልማት የበለጠ ለአካባቢ ወይም ለሀገር አቀፍ ችግሮች መፍትሄ በማግኘት ወደ ዘላቂ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ንግዶች መቀየር ነው ብለዋል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ ያሉ የፈጠራ ባለሙያዎችን ያሰባሰበው 10ኛው ብሔራዊ ዓመታዊ የሳይንስ እና ኢንጂነሪንግ ዐውደ ርዕይ ላይ ለተሳተፉ የምስክር ወረቀት እና በየደረጃው ተወዳድረው ላሸነፉ ተሳታፊዎች የማበረታቻ ሽልማቶችን በመስጠት ተጠናቋል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች