+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የኢትዮጵያ - ሩሲያ መንግስታት የኢኮኖሚ ፣ የሳይንስ እና የቴክኒክ ትብብር እና ንግድ የጋራ ኮሚሽን 9ኛ ስብሰባውን በሞስኮ አካሄደ።

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በግብርና ፣ በኢነርጂ ፣ በኢንዱስትሪ ፣ በትራንስፖርት ፣ በጤና አጠባበቅ ፣ በትምህርት ፣ በሳይንስ ፣ በባህል እና በስፖርት ውስጥ ተስፋ ሰጪ የትብብር እና የጋራ ተጠቃሚነት ላይ ተወያይተዋል።

በስብሰባው ላይ በታህሳስ 8 ቀን 2022 በሸራተን አዲስ በተካሄደው የጋራ ኮሚሽኑ 8ኛ የጋራ ጉባኤ ላይ የተደረጉ ውሳኔዎች አፈፃፀም የተገመገሙ ሲሆን ውጤታማ ሆነው እንዲፈጸሙ በሁለቱም ወገኖች ገንቢ ምክሮች ቀርበዋል።

በኢትዮጵያ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በቴክኖሎጂ፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በዲጅታል ግብይት፣ በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ፣ በኢነርጅ፣ በማዕድንና ሜታሉርጅ መስኮች ውስጥ አዳዲስ የትብብር ማዕቀፎች እየተተገበሩ መሆናቸው ለኢትዮጵያና ለሩሲያ የንግድና ኢንቨስትመንት ክበቦች እያደገና እየሰፋ የሚሄድ ተስፋ ሰጪ የትብብር ዕድል እየተፈጠረ መጥቷል ብለዋል።

ስምምነቱ ከኢኮኖሚ እስከ ፋይናንስ እንዲሁም ከኢነርጂ ቴክኖሎጂ እስከ ትራንስፖርት ድረስ ያለው የሁለትዮሽ ግንኝነትና ትብብር ማጠናከር እና ማስፋት ለሁለቱም ሀገራት ህዝቦች የጋራ ጥቅም ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉር ውስጥ በጣም አስፈላጊ መሆኗን የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ማክሲም ሬሼትኒኮቭ ጠቁመዋል።

በባቡር ፕሮጄክቶች እና በፋርማሲዩቲካልስ ውስጥ በሩሲያ እና በኢትዮጵያ መካከል ትብብርን ለማዳበር ትልቅ አቅም እንዳለው ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።

የሩሲያ የውጭ ንግድ መጠን ከኢትዮጵያ ጋር በ 2024 ከ 2023 ጋር ሲነጻጸር በ 50 በመቶ ጨምሯል ፣ በ 2025 ደግሞ በሦስት እጥፍ ማደጉ በውይይቱ ላይ ተገልጿል።

ከ2013-2017 ዓ.ም ጊዜ ውስጥ የተፈረመውን የሳይንሳዊ ጥናትና ትብብር ማራዘሚያ ፕሮቶኮል በሁለቱ ጣምራ ሰብሳቢወች ተፈርሟል።

የኢትዮጵያ-ሩሲያ የመንግሥታት የኢኮኖሚ ፣ የሳይንስ ፣ የቴክኒክ እና የንግድ ትብብር የጋራ ኮሚሽን በስብሰባው የተስማሙበትን ቃለ ጉባኤ በማፅደቅ እእንዲሁም በሁለቱ ሀገራት መካከል ሲደረግ የቆየውን የሁለትዮሽ የንግድ ድርድር ውጤት በመፈራረም ኢትዮጵያ ወደ አለም ንግድ እንድትገባ ለማድረግ የተያዘውን ጥረት በእጅጉ የሚደግፍ ይሆናል።

በ 2026 በኢትዮጵያ የጋራ የመንግስታት ኮሚሽን 10 ኛ ጉባኤ ለማድረግ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ