+251118132191
contact@mint.gov.et
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከማስተርካርድ ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችል የአጋርነት ፊርማ ሥነሥርዓት አካሄደ።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ እና የምስራቅ አፍሪካ ማስተርካርድ ኮርፖሬሽን ሥራ አስኪያጅ ሚስተር ሸህሪያር አሊ (Mr. Shehryar Ali, Country Manager East Africa-Mastercard) ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የአጋርነት የምስክር ወረቀት ፊርማ ሥነሥርዓት ተካሂዷል፡፡
መቀመጫውን ምስራቅ አፍሪካ ላይ ያደረገ ማስተርካርድ ኮርፖሬሽን የግሎባል ፔይመንት ኔትዎርክ ግብይቶች ስነምዳርን በማመቻቸት (Enabling Global Payment Network Transactions) ዓለም አቀፍ ካርዶችን መጠቀም የሚያስችል በሰው ሠራሽ አስተውሎት የተደገፈ የአቅም ግንባታ ሥራዎች ላይ በአጋርነት እየሠራ ያለ ዓለም አቀፍ ተቋም ነው፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በሀገራችን ፈጣን የሆነ ሁለንተናዊ እድገት ለማስመዝገብ በዲጂታል ዘርፉ ላይ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን አስገንዝበዋል።
ዘመኑን የዋጀ የዲጂታል ስነምህዳር መገንባት ዓላማችን ነው ያሉት ሚኒስትሩ በሀገራችን የዲጂታል ዘርፉን ለማሳደግ ከሀገር ውስጥና ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብርና በአጋርነት የሚሰሩ ስራዎች ትኩረታችን ናቸው ብለዋል።
የምስራቅ አፍሪካ ማስተርካርድ ኮርፖሬሽን ሥራ አስኪያጅ ሚስተር ሸህሪያር አሊ (Mr. Shehryar Ali, Country Manager East Africa-Mastercard) በኢትዮጵያ የዲጂታል ዘርፍ ላይ በአጋርነት ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል።
የአጋርነት የምስክር ወረቀት ፊርማው ዋና ትኩረቱ የዲጂታል ቱሪዝም በኢትዮጵያ የዲጂታል ክፍያዎች ለማበረታታትና ለማቀላጠፍ ሲሆን ዲጂታል ፋይናንሺያል ስርአት ሥነምህዳርን ማስፋትና ከአለማቀፍ ስርአት ጋር የማስተሳሰር አጋርነት ከኢትዮጵያ ተቋሞች ጋር ተያይዞ የአቅም ግንባታ ሥራዎችን ለመስራት ፕሮጀክቱን በይፋ ለማስጀመርና ለማስተዋወቅ ነው።
የአጋርነት የምስክር ወረቀት ፊርማ ስነ ሥርዓቱ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሙሉቀን ቀሬ፣ ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች እና ከማስተርካርድ የምስራቅ አፍሪካ ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች