+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የእስራኤል ኢምባሲ ጋር በጋራ ለመስራት በሚያስችሏቸው ጉዳዮች ላይ መከሩ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ዶ/ር አቭረሃም ንጉሴ ጋር በኢኖቬሽን ሳምንት ላይ በጋራ ለመስራት መክረዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ የኢትዮጵያ መንግስት ለኢኖቬሽንና ለስታርታፕ በሰጠው ልዩ ትኩረት ዘርፈ ብዙ ውጤቶች መመዝገባቸውን አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያና የእስራኤል ትብብርና ትስስር ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው በኢኖቬሽንና በስታርታፕ ስነምህዳር ግንባታ ላይ ሰፊ ልምድ ካላት ከእስራኤል ሀገራችን ብዙ አቅሞችን ትጋራለች ብለዋል።

በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ዶ/ር አቭረሃም ንጉሴ በኢትዮጵያ ያ የወጣት ኃይሉን አቅም በማጎልበት በኢኖቬሽንና በስታርታፕ ዘርፍ ላይ እዲሰማሩ በትብብር እንሰራለን ብለዋል።

በኢኖቬሽን ሳምንት ላይ በጋራ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በቀጣይ አጠናክሮ ለማስቀጠል ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው አንስተዋል።

በዘርፉ ላይ በትኩረት ለመስራትና የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት በትብብር የሚሰሩ ስራዎች ወሳኝ ሚና እንዳላቸው በምክክሩ ላይ ተነስቷል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ