+251118132191
contact@mint.gov.et
የኢኖቬቨንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር ሴም ፋብሪዚ (Sem Fabrizi) በጽ/ቤታቸው ተቀብለው በጋራ ለመስራት በሚያስችሏቸው ጉዳዮች ላይ መከሩ፡
የኢኖቬቨንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከጣሊያን ኤምባሲ እና ከልማት ትብብር ኤጀንሲ (AICS) ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ የስታርታፕ ሰነምህዳርን ለማጎልበት የሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
የኢኖቬቨንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በኢትዮጵያ የስታርታፕ ስነምህዳር ግንባታ ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን አስገንዝበዋል፡፡
ለሀገራችን ኢኮኖሚ እድገት የቴክኖሎጂ ሽግግርና ስታርታፕ ወሳኝ ሚና አለው ያሉት ሚኒስትሩ ሀገራችን ከጣሊያን መንግስት ጋር የጠበቀ የሁለትዮሽ ትብብርና ትስስርን በማጠናከር በልማቶቻችን ላይ በጋራ እንሰራለን ብለዋል፡፡
የጣሊያን መንግስት የኢትዮጵያ ስታርታፕን ለመደገፍ የጀመራቸውን ስራዎች ከግብ ለማድረስ የሁለትዮሽ አስፈፃሚ ኮሚቴ እንደሚዋቀርና ወደ ስራ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር ሴም ፋብሪዚ (SEM Fabrizi) ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር ለሚሰሯቸው ስራዎች ስኬት ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
የኢትዮጵያን የልማት ግቦች በተለይም በቴክኖሎጂ እና በዲጂታል ዘርፎች ለመደገፍ
የጣሊያን ትብብር ስትራቴጂ ቁልፍ አካል መሆኑን በውይይቱ ላይ ተነስቷል፡፡
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች