+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

11,500 የሳይንስና ቴክኖሎጂ የጽንሰ ሐሳብ አቻ ስያሜዎችን ከብያኔዎቻቸው ጋር የያዘ አዲስ መዝገበ-ቃላት መጽሐፍ ተመረቀ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሳይንስ አካዳሚ በጋራ በመተባበር አጠቃላይ ከ30 በላይ የሙያ ዘርፎች ከ90 በላይ ከከፍተኛ ትምህርት፣ ከምርምር ተቋማት እና ከሳይንስ አካዳሚ የተመረጡ ዕውቅ ባለሙያዎች የተሳተፉበት 11,500 አዲስ የሳይንስና ቴክኖሎጂ መዝገበ-ቃላት መጽሐፍ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አዳራሽ በርካታ ተሳታፊወች በተገኙበት ተመርቋል፡፡

በመጽሐፉ ምረቃ ሥነሥርዓት ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ የሳይንስና ቴክኖሎጂ (እንግሊዘኛ-አማርኛ) መዝገበ-ቃላት መጽሐፍ ሕትመት ተከናውኖ ለምረቃ መብቃቱ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍን በመረዳት ወደ ተግባር ለመለወጥ ለሚደረገው ጥረት ትልቅ ፋይዳ እንዳለው አስገንዝበዋል፡፡

የሳይንስና ቴክኖሎጂ መዝገበ-ቃላት በቀጣይ በብዙ የሀገራችን ቋንቋዎች እየተተረጎመ ተደራሽ እንዲሆን የማስቻል ሥራ ከኢትዮጵያ የሳይንስ አካዳሚ እና ሌሎች መሰል የምርምር ተቋማት ጋር መሠራት እንዳለበት በአፅንኦት ገልፀዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሙሉቀን ቀሬ መዝገበ-ቃላቱ በአለማችን ላይ እየረቀቀ የመጣውን የሳይንሳና ቴክኖሎጂ እድገት ከራስ አውድ ጋር በማስማማት በሀገር አቀፍ ደረጃ በቀላሉ ለማዳረስ ጠቃሜታው የጎላ ነው ብለዋል፡፡

ለፍሬ የበቃው የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ መዝገበ ቃላት እጅ ለእጅ ተያይዞ ዕውቀትን እና ኢኖቬሽንን ለማሳደግ ከማገዙም በላይ፤ በሳይንሳዊ ዕውቀት እና በኢኖቬሽን ላይ ተመሥርቶ የራሱን የወደፊት አቅጣጫ ለመንደፍ እና ለመቅረጽ የሚችል የተማረ ማኅበረሰብ ለመገንባት በተቋማቱ ዘንድ ያለውን ቁርጠኝነት ያረጋግጣል።

የሳይንስ አካዳሚ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር በላይ ካሳ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ተልእኳችን በመላው ኢትዮጵያ የሳይንስን ባህል፣ ዕውቀትን እና ኢኖቬሽንን ማስፋፋት ነው ብለዋል፡፡

የፕሮጀክት ውጤት የሚቆጠር ሳይሆን ዕውቀትን ለማስፋፋት፣ ፈጠራን ለማነቃቃት እና ማኅበረሰባዊ ዕድገትን ለማፋጠን ላለን ቁርጠኝነት ሕያው ምስክር መሆኑን አንስተዋል፡፡ በምረቃ ስነ ስርአት ተካፋይ የነበሩ እና በመጽሀፉ ዝግጅት ስራ የተሳተፉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ብሎም የሀገራችን አንጋፋ ምሁራን ይህ ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መጽሀፉን በማሳተም በቀጥታ ካደረገው እገዛ በተጨማሪ የሳይንስና ቴክኖሎጂ የጽንሰ ሐሳብ አቻ ስያሜዎችን ከብያኔዎቻቸው ጋር የያዘ አዲስ መዝገበ-ቃላት ውስጥ ያሉ ዕውቀቶች በቀላሉ በየሁሉም ሰው ቤት እንዲገቡ ለማስቻል የሞባይል መተግበሪያ ያለማ መሆኑን በመጽሐፉ ምረቃ ሥነሥርዓት ላይ ተገልጿል፡፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ