Minister's Message Minister's Message

Videos

>> watch more videos here

News News

ባለፈው አንድ አመት በኢትዮጵያ ውስጥ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ መሰረት ሊሆኑ የሚችሉ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክሎጂ ሚኒስቴር የባለፈው አንድ አመት የስራ እንቅስቃሴውን የተመለከተ ማብራሪያ ለጋዜጠኞች ሰጥቷል፡፡

የጀርመኑ ሲመንስ ኢንጂነሪንግ ካምፓኒ በኢትዮጵያ ‹‹የሲማቲክ አውቶሜሽን›› ማዕከል ሊከፍት ነው፡፡

በአውሮፓ ግዙፍ የሆነው የጀርመኑ የኢንደስትሪያል ማኑፋከቸሪንግ ካምፓኒ (ሲመንስ) ስራ አስኪያጅ ጆይ ኬሰር ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂ.) ጋር በኢትዮጵያ የጀርመን የቴክኖሎጂ ማዕከል መክፈት በሚቻልበት ዙሪያ መክረዋል፡፡

ብሎክ ቼይን ምንድነው? ቢትኮይንስ?

ብሎክቼን በሚሊየን የሚቆጠሩ የኮምፒውተር መረጃዎችን ባልተማከለ መልኩ የሚመዘግብ የብሎክ ጥርቅም የሖነ ቴክኖሎጂ ነው፡፡ ይኸ ቴክኖሎጂ በባንኮች እጅ የሚገኘውን እና በመንግሥታት ግምጃ ቤት ቁጥጥር የሚደረግበትን የገንዘብ ዝውውርና የመረጃ ፍሰት ያልተማከለ ለማድረግ እቅድ አለው። ከዚህ በተጨማሪ ከገንዘብ ዝውውር እስከ የመሬት ባለቤትነት ምዝገባ ያሉ ሥራዎችን ሊከወንበት እንደሚችል ተስፋ የተጣለበት ቴክኖሎጂ ነው፡፡ የማይሳሳት፣ የማይሰረዝ እና የማይጭበረበር በሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት የማይዘረፍ የአሰራር ሥርዓት ያለው ቴክኖሎጂ ነው፡፡ በተለይ በአፍሪካ ምድር አጨቃጫቂና የግጭት መንስኤ የሆነውን የመሬት አስተዳደርን በመመዝገብ ችግሩን ይፈታል ተብሎ ይታመንበታል፡፡ ይህ በብሎክ ቼይን ቴክኖሎጂ የተመዘገበ የመሬት አስተዳደር ስርዓት ደግሞ በሁሉም ኮምፒውተሮች ተመዝግቦ ስለሚገኝ በኃላፊዎችና በሰራተኞች ከሚደርስበት መጭበርበርና ከሶስተኛ ወገን ስርቆት ይገጥመዋል ተብሎ የማይሰጋበት ከስርቆት የፀዳ ያደርገዋል፡፡ ለምሳሌ በብሎክቼይን የተመዘገበ አንድ መሬት በሙስና ለሌላ ሰው ቢተላለፍ መረጃው ኮፒ ሆኖ በአለም ላይ ባሉ ኮምፒውተሮች ስለሚቀመጥ የትም ቦታ ላይ ይህ ስራ እንደተሰራ ስለሚነግረን ሙሰኞችን ለመቆጣጠር ያስችላል፡፡ ከአፍሪካ ውስጥ ሩዋንዳ ወደዚህ ቴክኖሎጂ በመግባት የመሬት አያያዝን ለማዘመን በቴክኖሎጂው ባለሙያዎች ጋር ስምምነት ተፈራርማ እንቅስቃሴ ማድረግ ጀምራለች፡፡ ኢትዮጵያ ደግሞ የብሎክቼን ቴክኖሎጂን ለማስተዋወቅ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴቶች ብቻ የተሳተፉበትን ቡድን እያሰለጠነች ትገኛለች፡፡

 

Service Channels

 

eServices.gov.et

apps.gov.et

data.gov.et

Selected Services Selected Services

Selected Resources Selected Resources

Related Links Related Links