+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የክቡር ሚኒስትሩ መልዕክት

የተከበራችሁ የድረ ገጻችን ተከታዮች

ለአንድ ሀገር  እድገትና ሁለንተናዊ ብልጽግና የኢኖቬሽናል ቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ የሚኖረው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ ስለሆነም የቴክኖሎጂና  ኢኖቬሽን ፖሊሲዎችንና እቅዶችን ከነባራዊው  ሁኔታው ጋር አጣጥመሞ ለመሄድ ያላሰለሰ ጥረት ይጠይቃል፡፡ በሃገራችን 1987 . ጀምሮ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ውጤት ለማምጣት ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎችና እቅዶች አውጥቶ በመተግበር መዋቅራዊ ለውጥ ማምጣት  እንዲቻል ጥረቶች ሲደረጉ ቆይቷል፡፡

ዘርፉን ማህበራዊና  ኢኮኖሚያዊ እድገት በማምጣት ድህነትን መቀነስ እንዲያስችል ቅድሚያ ተዋንያኑን የማብቃት ሰራ አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት ሲፈጸም ቆይቷል፡፡ በመሆኑም ለታቀደው ለውጥ የሚውል ቴክኖሎጂ ከኢንዱስትሪው ፍላጎት በመነሳት ማፈላለግ፣ ማቅረብ፣ መቅዳትና ማላመድ የሚችል ብቃቱ የተረጋገጠ የሰው ሃይል ለመገንባት የመገንባት ጥረት ሲደረግ ቆይቷል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን አገራዊ ለውጡን ተከትሎ የተነደፈውን የአገር በቀል የኢኮኖሚ አቅጣጫ ለማገዝ በአዋጅ ቁጥር 1097/11 መሰረት በአዲስ መልክ እንዲደራጅ ተደርጓል፡፡ አዲሱ አደረጃት በቴክኖሎጂ ዘርፍ ወጥነት ያለው ፖሊሲና ስትራቴጂ በማውጣት ለታሰበው አገራዊ ልማት የሚጠበቅበትን ሚና በተገቢ እንዲወጣ አዲስ አቅም አስገኝቶለታል፡፡ በተፈጠረለት አዲስ አቅም ከአገር በቀል ልማት አቅጣጫ የተቀዳ የአስር ዓመት የዘርፉን እቅድ አውጥቶ በአጭር ጊዜ ወደ ስራ መግባት ችሏል፡፡

ለተዘጋጀው አዲስ የልማት አቅጣጫ መሳካት የዲጅታል ቴክኖሎጂን መጠቀም ወሳኝ አቅም ተደርጎ ተለይቷል:: በመሆኑም ከአገር በቀል የኢኮኖሚ አቅጣጫ የተቀዳ፣ የአስር ዓመት እቅዱን የሚያሳካነና ዘርፉን የሚያጠናክር አካታች የድጅታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጅ ተዘጋጅቷል፡፡ ይህ የዲጅታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ አገር በቀሉ የኢኮኖሚ ልማት እቅድን በማሳካት አካታች ሀገራዊ ብልፅግና የሚያረጋገጥና የእስካሁን ስኬቶቻችንነን ወደ አዲስ የእድገት ምእራፍ የሚያስጉዝ ማዕዘን ነው፡፡

ይህ መከናወን የቻለው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና በዘርፉ የጠራ አመለካከት የያዘ የለውጥ አመራር በመምጣቱና በቂ ድጋፍ ማድረግ በመቻሉ ነው፡፡ በተሰጠው ትኩረት ልክ ውጤት ለማምጣት አዳዲስ አሰራሮችን በመዘርጋት፣ መስራት ይጠበቅብናል፡፡

የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፉ የስራ እድል በመፍጠር፣ኑሮን በማሻሻል፣ አሰራርን በማሳለጥ የአኗኗርን በመቀየር አስተዋጽኦ እንዲያደርግ እየሰራን እንገኛለን፡፡ የግልም ሆነ የመንግስት አገልግሎቶች ዜጋው ባለበት ሆኖ እንዲገለገል ምቹ ከባቢያዊ ሁኔታ በመፍጠር ላይ እንገኛለን፡፡

የተዘጋጀውን የድጅታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ ትግበራና የኤሌክትሮኒክ ትራንዛክሽን አዋጅ ይዘትና አፈጻጸም ውጤት ለዜጎች ለማሳወቅ አመች የመረጃ አውታር መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡ ስለሆነም ይህን ድረ ገጽ  በአዲስ መልክ አልምተናል፡፡  ከድረ ገጻችን አስፈላጊ መረጃዎችንና ወቅታዊ ጥቆማዎችን በመውሰድ፣ በመጠቀም በማዳበርና ግብረ መልስ በመስጠት ለስራችን ስኬት የበኩላችሁን እንድትወጡ አደራ እላለሁ፡፡

በለጠ ሞላ ጌታሁን (ዶ/ር)

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ