+251118132191
contact@mint.gov.et
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ጋር በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን ውጤታማነት ለማጠናከር እና የኢ-ሰርቪስ አገልግሎቶችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ነው።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ሚኒስቴር መስሪያቤታችን በዲጀታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ በዋናነት ከያዛቸው ስራዎች ውስጥ የዲጂታል ኢኮኖሚውን ለማሳለጥ የሚያስችሉ አስተማማኝና ፈጣን የዲጂታል አገልግሎቶችን በሁሉም ስፍራ ለተጠቃሚው እንዲደርስ ማድረግ አንዱ መሆኑን በስምምነቱ ላይ ገልጸዋል።
ይህንን ለማሳካት የኢኖቬሽን ስነ ምህዳርን ምቹ በማድረግ የሀገሪቱን ልማት ቀጣይነት ለማረጋገጥ ዘርፉን ማጠናከር የሚችሉ ስራዎችን ከኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ጋር በጋራ መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዳግማዊ ሀይሊዬ ተቋማቸው ለኢትዮጵያ ዘላቂ ልማት የበኩሉን አስተዋፅዖ በማበርከት በኢትዮጵያ ቀዳሚ የፖስታ አገልግሎት መሆኑን ተናግረዋል።
ድርጅቱ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም አስተማማኝ፣ ተደራሽና ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎቶችን ለደንበኞች ለመስጠት የዲጂታላይዜሽን ትብብሩን ማስፋት አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
የዲጂታል አሰራሮችን ተግባራዊ ለማድረግ እና ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት የኢኮኖሚ እድገትን ለማስመዝገብ የተጀመሩ እንቅስቃሴዎችን ውጤታማ ለማድረግ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሰፊ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ይገኛል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች