+251118132191
contact@mint.gov.et
"የኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፓርክ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ግንባታ ውስጥ ሚናውን ለመወጣት የሚያስችሉ የቴክኖሎጂ ተቋማት በውስጡ እየተደራጁ ነው።" ዶ/ር በለጠ ሞላ
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ስር የሚገኙ ተጠሪ ተቋማትን የስራ እንቅስቃሴ በመጎብኘት ላይ ናቸው። በዛሬው እለት ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል የማድረግ ርዕይ በመያዝ እየሰራ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፓርክን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ በፓርኩ ውስጥ ከሚገኙ ማለትም የፓወር፣ የኢንተርኔት፣ የውሃና መሰል መሰረተ ልማቶችን እንዲሁም በፓርኩ ከሚገኙ የቴክኖሎጂ ተቋማት መካከል IE Networks፣ RedCloud፣ MK Digital Security Solutions PLC፣ Uminers Datacenter፣ XDMT Datacenter እና የኮርፖሬሽኑ ዋና መስሪያ ቤት የስራ እንቅስቃሴ ተጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ የኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፓርክ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ግንባታ ውስጥ ሚናውን ለመወጣት የሚያስችሉ የቴክኖሎጂ ተቋማትን በውስጡ እያደራጀ ነው ብለዋል።
በፓርኩ ከዚህ በፊት ይነሱ የነበሩ የመሰረት ልማትና ምቹ የስራ ከባቢ አለመሟላት ችግሮች ተቀርፈው በውስጡ ለመሰማራት የሚፈልጉ የግል ዘርፍ የቴክኖሎጂ ተቋማትን ጥያቄ ለመመለስ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች የሚበረታቱ ናቸው ብለዋል።
ፓርኩ ትልቅ የሀገር ኢኮኖሚ አቅም በመሆኑ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተጠሪ ተቋማት እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በትብብር በመስራት የዕውቀት ሽግግር ማዕከል ሆኖ እንዲወጣ በትኩረት መሠራት እንዳለበትም ተናግረዋል።
ሌላኛው MK Digital Security Solutions PLC (MK DSS) የስማርት ካርድ ህትመት ፋብሪካ በጉብኝቱ የታየ ሲሆን ድርጅቱ ወደ ስራ ሲገባ እንደ ATM card, Sim card, digital ID card ላሉ አገልግሎቶች የሚውሉ እና ሌሎች ካርዶች ለሀገር ውስጥ ገበያ የሚያቀርብ ይሆናል። ፋብሪካው ምርቱን አለማቀፍ ስታንዳርዶችን በማሟላት በስፋት ለማምረት ዝግጁቱን ጨርሶ ማምረት መጀመሩ በክቡር ሚኒስተሩ ተበረታቷል።
ድርጅቱ ኢትዮጵያ ለስማርት ካርዶች ህትመት የምታወጣውን የውጭ ምንዛሬ ከማስቀረት ባለፈ የቴክኖሎጂ ሽግግርና የስራ እድል ከመፍጠር አንጻር በስሩ ከ100 በላይ ስራተኞችን በመቅጠር እየሰራ ሲሆን እስካሁን ከ1 ሚሊዮን በላይ የፋይዳ (Digital ID) ካርዶችን ማሳተሙ እና ከሁለት ባንኮች ጋርም በመስራት ላይ መሆኑ በጉብኝቱ ተነስቷል።
ሌላው በፓርኩ ውስጥ የሚገኘው የቴክኖሎጂ ተቋም RedCloud በኢንተርፕራይዝ መተግበሪያ ልማት፣ የሶፍትዌር ትግበራ፣ የደንበኛ ድጋፍ፣ የክላውድ አገልግሎት፣ የPOS ክፍያ መግቢያ፣ የስልጠና መሰል ስራዎች የሚሰራ ሲሆን በመላው ኢትዮጵያ በሚገኙ 12 ከተሞች አገልግሎቱን ተደራሽ ማድረጉ ታይቷል።
ተቋሙ ባለ ኮከብ ደረጃ ያላቸው ሆቴሎች፣ ሱፐርማርኬቶች እና ምግብ ቤቶች ጨምሮ ከ6,000 በላይ ደንበኞች ያሉት ሲሆን ከ130 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል ፈጥሯል።
ሌላኛው IE Networks ከኢንተርፕራይዝ ኔትወርክ አገልግሎት እና ከቢዝነስ አውቶሜሽን ኢንተለጀንስ እስከ ስማርት መሠረተ ልማት እንዲሁም የክላውድ አገልግሎት ባሉት ዘርፎች ላይ የሚሰራ ሲሆን በአለም አቀፍ ደረጃ የቴክኖሎጂ መፍትሄዎች እና አገልግሎቶች አቅራቢ ሲሆን በአፍሪካ ውስጥ የንግድ እንቅስቃሴን የሚቀይር ድርጅት ለመሆን አቅዶ እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።
ይህ ተቋም ለዜጎች የስራ እድል ከመፍጠር አንጻር በስሩ በሚገኙ 4 ድርጅቶች ከ200 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፍጠሩ ተወስቷል። በተጨማሪም በፓርኩ የታለንት ፕሮግራም ለመተግበር የሚያስችለውን አለም ዓቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የስልጠናና ፈተና መስጫ ማዕከል አደራጅቶ ወደ ስራ ገብቷል።
በጉብኝቱ ላይ የፓርኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሄኖክ አህመድ ፓርኩ የውጭ ኢንቨስትመንት ለመሳብ፣ ለኢትዮጵያውያን ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር፣ ከኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጋር የተገናኙ ምርቶችን እና አገልግሎቶችን ወደ ውጭ በመላክ ኢትዮጵያ በዓለም ዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ ተዋናይ እንድትሆን የሚያስችሉ አበይት ስራዎችን በመስራት የራሱን አስተዋጽኦ ከማበርከት ባለፈ በዘርፉ አርዓያ ለመሆን በትጋት በመሰራት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በመጨረሻም ፓርኩ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኢንተርፕራይዞች፣ በአካዳሚክ እና በምርምር ተቋማት መካከል የእውቀት ትስስርን ለማዳበር የሚያስችሉ ስራዎችን በመስራት ፓርኩ ለሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ ከፍተኛ አሰተዋጽኦ እንዲኖረው ቀጣይነት ያለው ስራ ይሰራል ብለዋል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች