+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

“የዲጅታል ኢትዮጵያ 2025 ስኬቶች በኢትዮጵያ የዲጅታል ትራንስፖርትና ሎጅስቲክ አገልግሎትን ለማስፋፋት ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል” ክቡር ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ

“በዲጂታል የታገዘ ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ” በሚል ርዕስ የሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት ተወካዮችን፣ የልማት አጋሮችን፣ የኢንዱስትሪ መሪዎችን እና ባለሙያዎችን የተሳተፉበት አውደ ጥናት ተካሂዷል።

በዝግጅቱ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ የዲጅታል ኢትዮጵያ 2025 ስኬቶች በኢትዮጵያ የዲጅታል ትራንስፖርትና ሎጅስቲክ አገልግሎትን ለማስፋፋት ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል ብለዋል።

ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በተመለከት የዲጂታል ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ስራዎች የዚህ ለውጥ እምብርት ናቸው ያሉት ሚኒስትሩ በዚህ ጊዜ ወደ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የተሸጋገረበት ምዕራፍ ነው፤ ይህም ሁሉን አቀፍ እና ቀጣይነት ያለው ዲጂታል እድገትን ለማምጣት ምቹ እንደሚያደርገው ገልጸዋል።

በስትራቴጂው ትግበራው፣ የዲጂታል ትራንስፖርት ፕላትፎርምን መዘርጋት እና እንደ ኦንላይን የነዳጅ ክፍያ፣ ስማርት ፓርኪንግ ፣ የትራፊክ አስተዳደር ስርዓቶችን የመሳሰሉ አገልግሎቶችን ማዘመንን ጨምሮ ትልቅ መሻሻሎች ባለፉት አመታት መታየታቸው ተገልጿል።

ዝግጅቱን ICT Association Ethiopia(ICT-ET) እና የተባበሩት መንግስታት ዓለም አቀፍ የንግድ ማዕከል(UNITC) ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ሲሆን በዝግጅቱ ላይ የተባበሩት መንግስታት ዓለም አቀፍ የንግድ ማዕከል (UNITC) የኢትዮጵያ አስተባባሪ አቶ ሳሙኤል ፈቃደ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና በአህጉሪቱ ያለውን የንግድ ስርአት በመቅረጽ ላይ መሆኑን ጠቅሰው ኢትዮጵያ እንደ መስራች አባልነቷ የመምራት ኃላፊነትም እድልም አላት ብለዋል።

ይህንን ውጤታማ ለማድረግ ዲጂታል ሲስተሞችን፣ ስማርት ሎጂስቲክስን እና ንቁ የግሉ ሴክተር ተሳትፎን ምቹ ፖሊሲ ያስፈልጋል ያሉት አቶ ሳሙኤል በዲጂታል የታገዘ ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ” ስራዎችን ለመስራት በዘርፉ የተሰማሩ የግል ተቋማትን፣የአጋር ድርጅቶችን እንዲሁም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር የጋራ ትብብር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

በተለይም በፈጠራ እና በፖሊሲ፣ በሕዝብ እና በግሉ ሴክተሮች መካከል ያለውን ርቀት በማስተካከል የአፍሪካን ዲጂታል እና የወደፊት የንግድ ልውውጥ ከፍ ለማድረግ ጠንከር ያለ ስራ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

አውደ ጥናቱ በትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ዘርፍ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችሉ አሰራሮችና ተሞክሮዎችን በመዳሰስ የኢትዮጵያን ቀጣይ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ዲጂታል ልማት የሚያሳውቅ ተጨባጭ የፖሊሲ ምክሮችን እና አጋርነቶችን ለማቅረብ ያለመ ነው።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ