+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

“ኢንተርኔት ለመላው ኢትዮጵያውያን" በሚል መሪ ቃል የዘንድሮው የኢንተርኔት ሶሳይቲ ፎረም በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ኮንፈረንሱ በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ የኢንተርኔት አስተዳደር ሀላፊዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ ሲቪል ማህበረሰብ፣ የቴክኖሎጂ ልሂቃን እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ከፍተኛ ሀላፊዎች የተሳተፉበት ሲሆን በበይነ መረብ ተደራሽነት፣ ዲጂታል ማካተት ላይ ያሉ ቁልፍ ተግዳሮቶች በመለየት ግንዛቤ ለመፍጠር እና በጥር 2025 ለሚካሄደው አለማቀፉ የኢንተርኔት ኮንፈረንስ ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ ያለመ ነው፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ መንግስት የግል ዘርፍ ተዋናዮች፣ ሲቪል ማህበረሰብ እና አካዳሚዎችን በማሳተፍ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በመደገፍ የዲጂታል ኢትዮጵያ ጉዛችንን እውን ልናደርግ ይገባል ብለዋል።

ኢንተርኔት የእድገት መሰረት፣ ግለሰቦችን፣ ማህበረሰቦችን እና ሀገሮችን የሚያገናኝ ድልድይ ሆኗል ያሉት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በገጠር ለሚገኙ አርሶአደሮች በየጊዜው የአየር ሁኔታ መረጃን ከመስጠት በተጨማሪ ወጣት የስራ ፈጣሪዎች የአለማቀፍ ገበያ እንዲያገኙ እና ትስስር እንዲፈጥሩ ያግዛል ብለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በዲጂታል ስነ-ምህዳር ግንባታ፣ የዲጂታል መሰረተ ልማት በማስፋፋት የህዝብ አገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል፣ የሳይበር ደህንነትን በማጠናከር፣ ለስራ ፈጠራ ምቹ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ዙሪያ መንግስት የአሰራር ስርዓትን ከመዘርጋት ጀምሮ በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር እና በኢትዮጵያ የኢንተርኔት ሶሳይቲ ፕሬዚዳንት የሆኑት ዶ/ር አስራት ሙላቱ ኢንተርኔት የአለም ዜጎች ኃይል እንዲፈጥሩ፣ እንዲተሳሰሩ እና አዳዲስ ነገሮችን እንዲፈጥሩ የሚያስችል መሳሪያ በመሆኑ አለምን እየቀየረ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

አያይዘውም በጤና፣ በትምህርት እና ሌሎች መሰል ጉዳዮች አንገብጋቢ ፈተናዎችን ለመፍታት ያለንን የኢንተርኔት የመጠቀም አቅም ማሳደግ፣ ተደራሽ ማድረግ፣ ብሎም ደህንነቱ የተጠበቀ የዲጂታል ስነምህዳር ለመፍጠር በጋራ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ