+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

በቴክኖሎጂ የጎለበተች አፍሪካን በጋራ ለመምራት Innovation Africa 2025 ጉባኤ የላቀ ድርሻ እንዳለው ዶ/ር በለጠ ሞላ ገለፁ።

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ በትምህርት ሚኒስቴርና በስራና ክህሎት ሚኒስቴር አስተባባሪነት April 28 - 30/2025 እየተካሄደ የሚገኘው የ Innovation Africa 2025 መድረክ የሁለተኛ ቀን ፕሮግራም የዲጂታል ቴክኖሎጂ ኢኮኖሚን በአፍሪካ ለማጎልበት የሚያስችል አለማቀፋዊ ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

ጉባዔው በአፍሪካዊያን ትብብር የዲጂታል ክህሎት እና የቴክኖሎጂ ፈጠራ እድገትን በማጎልበት በዓለም ተወዳዳሪ ለመሆነና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ያለመ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በዓለማችን እውቀት የልማት ምንዛሪ በሆነበት ዘመን ወጣቶቻችንን የዲጂታል ቴክኖሎጂ እውቀትን ማስታጠቅ ምርጫ ሳይሆን ግዴታ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የወጣት አፍሪካውያን የወደፊት የስራ ስምሪት በቴክኖሎጂና በዲጂታል ዘርፍ ላይ የተመሰረተ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ሁሉም ዜጎች አስተዳደጋቸው እና መልክአ ምድራዊ አቀማመጥቸው ምንም ይሁን ምን እኩል የዲጂታል መንገዶችን እና የመማሪያ መድረኮችን እንዲያገኙ ማድረግ የአፍሪካዊያን የጋራ የሆነ ሀላፊነት ነው ብለዋል።

የአፍሪካን የተማሪ አቅም በSTEM የትምህርት መስክ መጎልበት አለበት ያሉት ሚኒስትሩ የአካዳሚክ ስኬትን የሚያበረታቱ ብቻ ሳይሆን ሂሳዊ አስተሳሰብን ችግር የሚፈቱ እና ፈጠራን በሚያበረታቱ የትምህርት ስርዓቶች ላይ ኢንቨስት መደረግ እንዳለበትም ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ በመንግስት እና በግሉ ሴክተሮች በተደረጉት የተቀናጀ እርምጃዎች የስታርታፕ እና የቴክኖሎጂ ፈጠራ ላይ ፈጣን ለውጥ እያመጣች ነው ያሉት ሚኒስትሩ ለሥራ ፈጣሪዎች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር፣ በኢንዱስትሪ፣ በአካዳሚዎች መካከል የአጋርነት መንፈስን ለማጎልበት እና የስታርታፖች እድገትን ለማሳለጥ ፖሊሲ ለማውጣት፣ የጋራ፣ ቁልፍ ተግዳሮቶችን ለመፍታት፣ ለዜጎቻችን አዳዲስ እድሎችን ለመክፈትና የፈጠራ እምቅ ችሎታን ለመጠቀም በትብብር መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል።

በአህጉራችን ውስጥ ፈጠራ እና ቴክኖሎጂን የሚያጎለብት ትብብርን ለማስፋት የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ቁርጠኛ መሆኑን የገለፁት ሚኒስትሩ በመደመር፣ በማብቃት እና በዘላቂነት ልማት የምትታወቀውን አፍሪካን የተሻለ የወደፊት ሁኔታ ለመገንባት እንተባበር ብለዋል።

ጉባዔው በዲጂታል፣ በትምህርት፣ በኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽንና ቴክኖሎጂ እና በአቅም ግንባታ ላይ የሚያተኩር ሲሆን የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሚኒስትሮች፣ እህትማማች የአፍሪካ ሀገራት ምክትል ሚኒስትሮች፣ አምባሳደሮች፣ የአለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች፣ የአካዳሚክ ምሁራንና ሌሎች የሚመለከታቸው እንግዶች እየተሳተፉበት ይገኛሉ፡፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ