+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

2ኛው ዙር የዲጂታል ፋይናሻል የክህሎት ዘመቻ ከ50 ሺህ በላይ ሴቶችንና ተማሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ ገለፁ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከትምህርት ሚኒስቴርና ከUNCDF ጋር በመተባበር በተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች በአዲስ አበባና በክልሎች የ2ኛ ዙር የዲጂታል ፋይናሻል ክህሎት ዘመቻ ማስጀመሪያውን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ።

ጋዜጣዊ መግለጫውን የሰጡት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስኬታማ ለማድረግ አካታች በሆነ የዲጂታል ክህሎት ላይ ሰፋፊ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸው ገልፀዋል።

በዲጂታል ቴክኖሎጂ ትግበራ ዙሪያ ኢትዮጵያ መሰረታዊ ለውጦችን እያደረገች መሆኑን ያብራሩት ሚኒስትር ዴኤታው የዲጅታል ልዩነትን በመፍታት የዜጎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ መሆኑንም ተናገረዋል።

የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን አካታች ለማረጋገጥ ከተለያዩ ተቋማትና ሙሁራን ጋር በትብብር መሰራት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚውን ለማጎልበት የሚያስችላትን መርሃ ግብር በመንደፍ የዲጂታል ክህሎት ክፍተትን ለመቅረፍ የሚያስችል የ5 ሚሊየን ኮደርስ ስልጠና ዕድልን ሁሉም መጠቀም እንዳለበት አሳስበዋል።

በአንደኛ ዙር 16 ሺህ ተማሪዎችን ተደራሽ ማድረግ የተቻለ ሲሆን የ2ኛው የዲጂታል ክህሎት ዘመቻው በአዲስ አበባ 5 በክልል 7 ትኩረት በተደረገባቸው አካባቢዎች ከ50 ሺህ በላይ ሴቶችንና ተማሪዎችን ተደራሽ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ