+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

13ኛው የአፍሪካ የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባዔ በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) እየተካሄደ ነው፡፡

በጉባዔው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና ከተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ‹‹ building our multi stakeholder digital future›› በሚል መሪቃል የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የፓርላማ አባል የሚሳተፉበት እና ሌሎች ዕርሰ ጉዳዮችን ያካተቱ የተለያዩ መድረኮች ተካሂደዋል፡፡

ጉባኤው የሳይበር ደህንነትና ወንጀል፣ ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ፣ የኢንተርኔት አስተዳደር፣ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ፣ የዲጂታል ሰባዊ መብቶች፣ ዘላቂነት፣ ሁለንተናዊ ተደራሽነት ሀጉራዊ ግኑኝነትን በመፍጠር ልምድ ለማጋራትና በጋራ ለመስራት ያለመ ነው፡፡

የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሰው ሀብት ልማት ስራ ስምሪትና የቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ስብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ የፓርላማ አባላት በዘርፉ ላይ ያሉ የህግና የቁጥጥር ማዕቀፎችን፣ መመሪያዎችን፣ አዋጆችን እና ፖሊሲዎችን በማውጣት ጉልህ እና የማይተካ ሚና ይጫወታሉ ብለዋል ።

ኢትዮጵያ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 የተሰኘውን አገራዊ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ ተግባራዊ ለማድረግ መስራት ከጀመረች አሁን 5ኛ ዓመቱን ያስቆጠረ ሲሆን የስትራቴጂው ትግበራው የኢኮኖሚውን እያሳደገ መሆኑን በኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜ የኤሌክትሮኒክስ የገንዘብ ልውውጥ ከባህላዊ ግብይት ወጥቶ ከ3 ትሪሊዮን ብር በላይ በኤሌክትሮኒካዊ የግብይት መካሄዱን አንዱ ማሳያ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

እስካሁን ከተገኙት የበለጠ የኢንተርኔት ጥቅማጥቅሞችን ማሳደግ እንዲቻል በተለይም እኛ አፍሪካውያን እንደዚህ ባሉ መድረኮች ተሰባስበን ተግባራዊ አቅጣጫዎችን ልናስቀምጥ፣ አፍሪካ ከአለም አቀፍ የኢንተርኔት ልማት ፍትሃዊ ተጠቃሚ እንድትሆን መሰራት እንዳለበት አንስተዋል፡፡

ጉባዔው የኢንተርኔት እና የዲጂታል ስራዎችን ለመፍታት የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን ያሰባሰበ ሲሆን በፖሊሲ ጉዳዮች ከአፍሪካ ዲጂታል የወደፊት የጋራ ራዕይ ጋር የተጣጣመ የህዝብ ፖሊሲዎችን ለመቅረጽ የሚያስችሉ ጉዳዮች ይዳሰስበታል፡፡

እየተካሄደ ያለው 13ኛው የአፍሪካ የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባዔው እስከ አርብ ቀን 13/2024 በተለያዩ አጀንዳዎች ተከፋፍሎ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ