+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ለሀገራችን ብሎም ለዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ እድገት መጎልበት የቴክናሎጂው ዘርፍ የላቀ ሚና እንዳለው ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ገለፁ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኖች የ2017 ዓ.ም የ9 ወር የእቅድ አፈፃፀም ውይይት አካሂደዋል።

ሀገራዊና ተቋማዊ የተከናወኑ የ2017 ዓ.ም የ9 ወር የዕቅድ የአፈፃፀም ሪፖርት በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ቀርቧል።

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ሀገራዊው የኢኮኖሚ ሪፎርም ይዞ በመጣው ለውጥ ወስጥ ሁሉም ዜጋ በቀጥተኛም ይሁን በተዘዋዋሪ የተሳተፈበት ስለሆነ የተሰሩ ስራዎችን ማወቅ ይጠበቅበታል ብለዋል።

የሚቀርቡ ሪፖርቶችን ከተለመደው አቀራረብ ወጣ ባለ መንገድ በጋራ ማየት ትርጉሙ ትልቅ ነው ያሉት ሚኒስትሯ ለሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገታችን ስንሰራ በመካከላችን ያሉ አላስፈላግ ግንቦችን በማፍረስ አንድ ሆነን ለአንድ ቤታችን የምንሰራበትን ዕድል ለመፍጠር መሆኑን ገልፀዋል።

አክለውም በከተሞች የዲጂታል አድራሻ ስርአት ልማት እና በሌሎችም ዘርፎች በቀጣይ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በጋራ አብረው እንደሚሰሩ ጠቁመዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ሀገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙና መንግስት ለቴክኖሎጂ የሰጠውን ትኩረት በመጠቀም በአለም ላይ ዘርፉ የፈጠረውን የኢኮኖሚ እድገት ግስጋሴ አካል ለመሆን በመሰረተ ልማት፣ በሰው ሀይል ግንባታ፣ የፖሊሲ፣ ስትራቴጂ፣ መመሪያ፣ ደንቦችን እና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ስራዎች መሰራታቸውን አስገንበዋል።

ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚውን በማጎልበት የሀገራዊ ውስብስብ የፋይናን ስርዓት ለመፍታት፣ ዜጎች ሀብትና ጉልበታቸውን ቆጥበው ባሉበት የተለያዩ አገልግሎትን እንዲያገኙና የስራ እድል በመፍጠር የዲጂታሉን እውቀት በማስታጠቅ የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ከፍተኛ አስተዋፆ እንዳስገኘም ተናግረዋል።

የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ ለሁለንተናዊ ኢኮኖሚ እድገት መሰረት ነው ያሉት ሚኒስትሩ ሁሉም በዘርፉ ላይ በመትጋት ዛሬ በተገኘው ውጤት ላይ በመደመር በቴክኖሎጂ የዘመነችና ለሌሎች ሀገሮች ምሳሌ የሆነች ኢትዮጵያን መገንባት ይጠበቅብናል ብለዋል።

ሪፖርቱም ትኩረት ያደረገው በአጠቃላይ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ አዝማሚያ ለኢትዮጵያ ያለው አንድምታ፤ በማክሮ ኢኮኖሚና ሪፎርም፤ በመሰረተ ልማት እና ፕሮጀክት ስራዎች፤ በዘላቂ ልማት፣ በማህበራዊ አካታችነትና ሁለንተናዊ ሉዓላዊነት፤ የሰላም፣ ዲፕሎማሲ እና ትብብር ስራዎች እንዲሁም በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዩች ዙሪያ ነበር፡፡

ተሳታፊዎች ሀገራዊውና ተቋማዊውን ሪፖርቱ በአንድ ላይ መቅረቡ ወሳኝ መሆኑን በመግለፅ ለተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎች ከፍተኛ አመራሩ የተብራሩ መልሶች የሰጡ ሲሆን በቀጣይ ሩብ አመት ሊሰሩ ይገባቸዋል በተባሉት የስራ ላይ አቅጣጫ በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ