+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ሽግግር ትልቅ እርምጃ ነው

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ሽግግር ትልቅ እርምጃ መሆኑን ሚኒስትሮች ተናገሩ፡፡

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)፣ የፍትህ ሚኒስትር ሀና አርዓያሥላሴ፣ የሰላም ሚኒስትር መሀመድ እድሪስ እና የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ፤ ማዕከሉ የመንግስት አገልግሎትን በከፍተኛ ሁኔታ የሚያቀላጥፍ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ማዕከሉ የተቀናጀ አገልግሎት ለተገልጋዩ መስጠት የሚያስችል ትልቅ ውጤታማ ስራ መሆኑንም ገልጸው፤ ማዕከሉን በማደራጀት ወደ ስራ መገባቱ በሀገሪቱ የታለመውን ለውጥ ለማምጣት ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡

ማዕከሉ ቅሬታ ይቀርብባቸው የነበሩ አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል በማስገባት የተቀላጠፈ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ትልቅ እርምጃ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ሽግግር ትልቅ እርምጃ መሆኑን ጠቅሰው፤ ለብዙ ግዜ በመንግስት ተቋማት የነበሩ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን እንደሚፈታ ተናግረዋል፡፡

ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጂን አቀናጅቶ የያዘ ትልቅ ተቋም መሆኑን ገልጸው፥ ሥራዎች በአግባቡ ከተመሩ ትልቅ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ያስመሰከረ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

መንግስት ለሰው ተኮር አገልግሎት የሰጠው ትኩረት የተግባር ማረጋገጫ ማዕከል እንደሆነ የጠቀሱት ሚኒስትሮቹ፤ ህብረተሰቡ ባልተንዛዛ ቢሮክራሲ እንዲሁም በተቀላጠፈ መንገድ አገልግሎት እንዲያገኝ የሚያደርግ ነው ብለዋል።

በአጠቃላይ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በሀገሪቱ የአገልግሎት አሰጣጥ እንደ ታሪክ እጥፋት የሚቆጠር ትልቅ ስራ መሆኑን ማስታወቃቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

አገልግሎትን ከማዘመን ባለፈ ተጠያቂነትን ለማስፈን የሚያስለው ማዕከሉ፤ ለጤናው ዘርፍ አገልግሎት አሰጣጥም ተሞክሮ የሚወሰድበት እንደሆነም አብራርተዋል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ