+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ብዝኃነትን የሃሳብ ምንጭ አድርጎ አካታችና አሳታፊ በማድረግ ለጋራ እድገት በጋራ መስራት ላይ የተያዘውን አቅጣጫ በቅጡ መረዳት ያስፈልጋል፡፡

አዲስ አበባ፡ ሚያዚያ 7/2017 ዓ.ም (ንቀትሚ) ኢትዮጵያ በብዝሃነት የምትታወቅ የተለያዩ አመለካከቶችና ፍላጎቶች የሚንፀባረቁባት ሀገር በመሆኗ ብዝኃነትን የሃሳብ ምንጭ አድርጎ አካታችና አሳታፊ በማድረግ ለጋራ እድገት በጋራ መስራት ላይ የተያዘውን አቅጣጫ በቅጡ መረዳትና ግንዛቤ መጨበጥበጥ ይገባል ሲሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ገለፁ፡፡

ሚኒስትሩ ይህን የገለፁት ዛሬ በተካሄደው የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት አመራርና ሰራተኞች የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀምና የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራ አፈፃፀም የውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ትልቅ አገርና ህዝብ እንዲሁም ትልቅ የመልማት አቅም ያላት ሀገር እንደመሆኗ በየትኞቹ አቅሞች ላይ ትኩረት ሰጥተን ብንሰራ በአጭር ጊዜ መበልፀግ እንችላለን የሚለው በአግባቡ ተለይተው ርብርብ እየተካሄደ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሩ በዚህም አምስት የእድገታችን ምሰሶ የሆኑ ዘርፎች እንደ ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክነሎጂ፣ማእድን፣ቱሪዝም፣ንገድና የመሳሰሉት ዘርፎች ላይ ርብርብ በማድረግ አመርቂ ውጤት እየታየባቸው ይገኛል ብለዋል፡፡

ዶ/ር በለጠ አያይዘው እንደገለፁት ኢኮኖሚያችን በቴክኖሎጂ መታገዝ ያለበት መሆኑንና ለዚህም ስትራቴጂ መነደፉን አንስተው የንግድ ስርዓቱ ከዚህ ጋር ተሰናስሎ መካሄድ እንዳለበት ገልፀው የኢኖቬሽና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር በጋራ የሚሰራቸውን ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ