+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የሀገራችንን የኢ-ኮሜርስ ንግድ በማጎልበትና በማስፋት ለዜጎች የስራ ዕድል ፈጠራ ያለውን ሚና ልንጠቀምበት ይገባል ዶ/ር ይሹሩን ዓለማየሁ።

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ የኢትዮጵያ ፖስታ ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፣ የግሉ ዘርፍ እና ሌሎች የከተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የኢ-ኮሜርስ አገልግሎትን ለማስፋት የሚያስችል መድረክ አካሂዷል።

መድረኩ የዲጂታል ግብይትን በማጎልበት ከኢትዮጵያ አልፎ በአፍሪካ አህጉር ተደራሽ የሚሆንና የስራ እድል ለመፍጠር የሚያስችለውን እድል ለመጠቀም የሚያስችል ስነምህዳር ለመፍጠር ያለመ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ ኢትዮጵያ የዲጂታል ቴክኖሎጂው በአለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ሚና ለመጋራትና ከዘርፉ ለመጠቀም የሚያስችል ስርዓትን በመፍጠር የዜጎችን ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ሰፋፊ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል፡፡

ሀገራችን በፖሊሲ እና በህግ ማዕቀፎች እና በቴሌኮሙኒኬሽን መሠረተ ልማት ዝርጋታ ላይ መንግስት ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ሀገራችን የዘርፉን ስነምህዳር በማሳለጥ የኢ-ኮሜርስ የገበያ ውድድር በማሳደግ ከዘርፉ የሚጠበቀውን የኢኮኖሚ እድገት ለማስመዝገብ በቅንጅትና በትብብር መሰራት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

በሀገራችን የኢ-ኮሜርስ የንግድ ሥርዓት የሀገራዊ የልማት መርሐግብርን ለማሳደግ፣ የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማጎልበት እና ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንድትሆን ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልፀዋል።

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ያስሚን ውሀረቢ ሀገራችን የንግዱን ዘርፍ ለሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገት ለመጠቀም የኢ-ኮሜርስ የንግድ ሥርዓት ላይ በትኩረት እየተሰራና ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አክለውም የኢ-ኮሜርስ የንግድ ሥርዓት በሀገር ደረጃ ተደራሽ ለማድረግና የሚፈለገውን አላማ ለማሳካት በሁሉም ማህበረሰብ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ በስፋት መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

በኢ-ኮሜርስ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ ግልጽ የሆነ የሕግ ማዕቀፍ ሥራ ማቋቋም፣ የኢኮሜርስ ኢንዱስትሪን በአይሲቲ መሠረተ ልማት ላይ ኢንቨስት በማድረግ መደገፍ ከባህላዊ የችርቻሮ ንግድ ውድድር መሠረቶች ይልቅ በቴክኖሎጂ ፈጠራ ውድድር ላይ ለማተኮር በትኩረት መሰራት እንዳለበት በመድረኩ ላይ ተገልጿል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ