+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ስኬታማነትን ለማረጋገጥና በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነች ሀገር ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን ዶ/ር ይሹሩን ዓለማየሁ ገለፁ

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሚመራ ሀገር አቀፍ የዲጂታል ቴክኖሎጂ እድገት ደረጃ አጥኝ ቡድን ተቋቁሞ ወደ ስራ ማስገቢያ መድረክ በሚኒስቴር መስሪያቤቱ ተካሂዷል፡፡

መድረኩ ሀገራችን በዲጂታል ኢኮኖሚ ያለበችበትን ደረጃ የዓለም ባንክ በሚጠይቀውን የ2025 ‘‘Gov tech maturity index online survey’’ መመዘኛ መስፈርት መሠረት በመገምገም እና ከሌሎች ዓለም አገራት ጋር ተወዳዳሪ እንድትሆን ለማስቻል ያለመ ነው፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሹሩን ዓለማየሁ የኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ስኬታማነትን ለማረጋገጥና በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነች ሀገር ለመገንባት በርካታ የመሠረተ-ልማት ግንባታ ማከናወኗን አስገንዝበዋል፡፡

የዲጂታል ቴክኖሎጂ ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ 2025ን ለማሳካት በተደረገው ጥረት ኢንቨስትመንትን በመሳብ፣ የሀገርን መልካም ገጽታ በማጉላት፣ ለዜጎች የስራ ዕድል ፈጠራ ማዋል እንዲቻል፣ በየዘርፉ ምቹ ስነምህዳር ለመፍጠር፣ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እቅዱ ያስመዘገበውን ውጤት በመለካት፣ ደረጃውን በማጥናት ለማረጋገጥ ቡድን ተደራጅቶ ወደስራ ገብቷል ብለዋል፡፡

አክለውም ሀገራችን በዲጂታል ኢኮኖሚ ልማት ከሌሎች ዓለም አገራት ጋር ያለንበት ደረጃ ተወዳዳሪ መሆኗን በ‘‘Gov tech maturity index online survey’’ መጠይቅ መመዘኛ መስፈርቶች መሰረት ለማረጋገጥ ጥናቱ ጥንቃቄ የተሞላበት፣ ትክክለኛ፣ እውነተኛና በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ሆኖ በጥንቃቄ ተሞልቶ እንዲቀርብ ሲሉ አሳስበዋል፡፡

በመድረኩ ገንዘብ ሚኒስቴር፣ ፍትህ ሚኒስቴር፣ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ ከተማና መሠረተ-ልማት ሚስቴር፣ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን፣ ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ፣ የኢንፎርሜሽን ደህንነት አስተዳደር፣ አርቲፊሻል ኢንቴሊጀንስ ኢንስቲትዩት፣ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፣ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም፣ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተወከሉ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተገኝዋል።

ቡድኑ ከፌደራል ተቋማት የተውጣጡ አባላትን ያካተተ ሲሆን ኢትዮጵያ በ‘‘Gov tech maturity index online survey’’ መጠይቅ በማዘጋጀትና በዓለም አቀፍ መመዘኛ መስፈርት መሰረት ሀገራችንን በዲጂታል ቴክኖሎጂ አገልግሎቶች ያለችበትን ደረጃ መፈተሸ፣ መገምገምና መረጃዎችን በማደራጀት የሚያቀርብ መሆኑን ተጠቁሟል፡፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ