+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ በቻይና ኢሲያን የአፍሪካ መንደር ማኔጅመንት ኮሚቴ ዳይሬክተር የተመራ ልዑካን ቡድን በቢሯቸው ተቀብለው በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መከሩ፡፡ =====

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ በቻይና ኢሲያን የአፍሪካ መንደር ማኔጅመንት ኮሚቴ ዳይሬክተር የተመራ ልዑካን ቡድን በቢሯቸው ተቀብለው በሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ የንግድና አገልግሎት ቅብብሎሽ ስርዓትን ለማዘመን በሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች ዙሪያ ለመስራት በጋራ መክረዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሹሩን ዓለማየሁ የሀገራችንን የዲጂታል ኢኮኖሚውን ለማጎልበት የአለም አቀፍ ኢኮኖሚ እድገት መዘወሪያ የሆነውን በሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ሰፋፊ ስራዎች መሰራታቸውን አስገንዝበዋል፡፡

ኢትዮጵያ ዘርፉን ለማጎልበትና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ከአጋር ድርጅትና ተቋማት ጋር የምታደርገውን የትብብር ስራን በትኩረት እንደምትተገብርና ምቹ ሁኔታዎች ለመፍጠር ጠንክራ እንደምትሰራ ገልፀዋል፡፡

የቻይና ኢሲያን የአፍሪካ መንደር ማኔጅመንት ኮሚቴ ዳይሬክተር በኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ የንግድና አገልግሎት ቅብብሎሽ ስርዓትን ለማዘመን በትብብር ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለቸው ገልፀዋል፡፡

በምክክሩም በቀጣይ የጋራ የሆነ ኮሚቴ በማቋቋም ወደ ስራ ሊያስገባ የሚችል የጋራ የሆነ የስምምነት ሰነድ በማዘጋጀት እንደሚፈራረሙ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ