+251118132191
contact@mint.gov.et
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፦
- የባዮና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ፣ የጂኦስፓሻል፣ የስፔስ፣ የቴክኖሎጂ እና ዲጂታል ኢኮኖሚ ልማትንና ተወዳዳሪነትን በቀጣይነት የሚያረጋግጡ፣ ፖሊሲዎችን፣ ስትራቴጂዎች፣ ሕጎችንና ፕሮግራሞች ይቀርጻል፣ ለአፈጻጸሙ ዝርዝር ከሀገራዊ የልማት አቅጣጫ ጋር የተጣጣመ መርሀ- ግብር ያዘጋጃል፤ በሚመለከተው አካል ሲጸድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፤
- ከሚመለካታቸው አካላት ጋር በመተባበር የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂ እና የኢኖቬሽን አጠቃቀም ባህል እንዲጎለብት የሚያስችል ፖሊሲ ያመነጫል፣ በሚመለከተው አካል ሲጸደቅም ተግባራዊ መደረጉን ይከታተላል፤የሀገሪቱ ሥርዓተ- ትምህርት እና ሥርዓተ- ሥልጠና ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት አንጻር መቃኘቱን ያረጋግጣል፤
- የሀገራዊ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ምርምርና ልማት ፖሊሲዎችን፣ ስትራቴጂዎችን እና ፕሮግራሞችን ያዘጋጃል፣ ያስፈጽማል፣ ለሀገሪቱ እድገት አስፈላጊ የሆኑ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ የጥናትና ምርምር መስኮችን ይለያል፤ ሀገራዊ የምርምር ፕሮግራሞችን ያስተባብራል፤
- በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ልማት የግል ዘርፉን ተሳትፎና ሚና ለማሳደግ የሚያስችል ሥርዓት ይዘረጋል፣ ለአፈጻጸሙ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፣ ለኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማትና ለፈጠራ ሥራዎች እድገት አስተዋጽኦ ላበረከቱ ግለሰቦችና ተቋማት ሽልማትና ማበረታቻ የሚሰጥበትን ሥርዓት ይዘረጋል፣ ተግባራዊም ያደርጋል፤
- ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎቶች ጥራታቸው፣ ደህንነታቸውና አስተማማኝ ነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን የሚያስችሉ ደረጃዎችን ይወስናል፣ ተግባራዊ መደረጋቸውንም ይቆጣጠራል፤
- በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ ተቋማትና ባለሙያዎች አቅም ግንባታን ይደግፋል፤ የሙያ ማህበራትንና የጥናትና ምርምር ተቋማትን ይደግፋል፣ ያበረታታል፤
- ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የቴክኖሎጂ ፍላጎት ለመዳሰስ፣ ተገቢ ቴክኖሎጂዎችን ለማፈላለግና በሥራ ላይ ለማዋል የሚያስችል ሥርዓት ይዘረጋል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
- ሀገር-በቀል ቴክኖሎጂዎችን ለማሻሻል፣ ለማሳደግና ለገበያ ለማቅረብ የሚደረጉ ጥናቶችን፣ የምርምርና ስርጸት ሥራዎችን ያበረታታል፣ ወደተግባር እንዲሸጋገሩ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፤ በፕሮቶታይፕ፣ ለባለድርሻ አካላትና ለማህበረሰቡ ተደራሽ ያደርጋል፤ ለኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ መዳበር የበለጠ አስተዋጽኦ ሊያደርጉ የሚችሉ ግለሰቦችን፣ የሙያ ማህበራትንና የጥናትና ምርምር ተቋማትን ያበረታታል፣ ይደግፋል፤
- በየዘርፉ በሽግግር የሚመጡ ቴክኖሎጂዎችን መረጃ ይመዘግባል፣የማጠቃለልና የማቀብ ሥራዎችን ያስተባብራል፣ ለቀጣይ ሥራ እንዲውሉ ያደርጋል፤
- የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ በተለይ የዲጂታል መሠረተ ልማቶች ለማስፋፋት የሚያስችሉ ፕሮግራሞችን በመቅረጽ ተግባራዊ ያደርጋል፤ ለሕዝብ አገልግሎት በመስጠት ላይ ያተኮሩ መሠረታዊ የአሠራር ሥርዓትና አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ የሚደገፉበትንና ለተጠቃሚዎች የተሻለ አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉበትን ሁኔታ መመቻቸታቸውን ያረጋግጣል፤ በአጠቃላይ የመንግስት አገልግሎት በቴክኖሎጂ የተደገፈና ቀልጣፋ እንዲሆን ይሰራል፣ ድጋፍ ያደርጋል፤
- የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ መረጃ ቋት ያደራጃል፣ መረጃዎችን ያጠናቅራል፤ ሀገራዊ የመረጃ አያያዝ ደረጃ ያወጣል፤
- ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የፌደራልና የክልል መስተዳደር ተቋማት የመረጃ ሥርዓትን ይገነባል፣ ያቀናጃል፤ ደህንነቱ የተጠበቀ የኢንፎርሜሽን መረብ የመዘርጋት ሥራን ይደግፋል፤
- ለተመረጡ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ምርምር የሚውሉ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ቤተ-ሙከራና የሰርቶ ማሳያ ማዕከላትንና የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ፓርኮችን በማቋቋም የሀገር ውስጥ የፈጠራ ክህሎት እንዲያድግ ድጋፍ ያደርጋል፤ለዚህም የሚያግዝ ስታርት አፕ ፈንድ እንዲቋቋም ያመቻቻል፤
- የጨረራና ጨረር አመንጪ ቁሶች አጠቃቀምና አወጋገድ ቁጥጥር ሥርዓት ተግባራዊ መደረጉን ይከታተላል፤
- ለክልሎች ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ተቋማት አቅም ግንባታ አስፈላጊውን የሙያና ቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል፤ በክልሎች መከናወን ያለባቸውን የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ተግባራትን በመለየት የጋራ መግባባት ተደርሶባቸው በየደረጃው ተግባራዊ እንዲደረጉ ያደርጋል፤ ተግባራዊ መደረጋቸውን ይከታተላል፤
- የፈጠራ ሀሳቦችን ወደ እሴት በመለወጥ ለሀገራዊ ብልጽግና የሚያደርጉት አስተዋጽኦ ውጤታማ እንዲሆን ይከታተላል፤
- ፪/ በሥራ ላይ ባሉ ሌሎች ሕጎች ለኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተሰጡ ሥልጣንና ተግባራት በዚህ አዋጅ ለተቋቋመው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተሰጥተዋል።
—
5 每页项目
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች
©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ