+251118132191
contact@mint.gov.et
በድጅታል ክህሎት የበለጸገ ማህበረሰብ በአገር አቀፍ ደረጃ እንዲፈጠር በሴቶችና ወጣቶች ላይ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ሲሉ ዶክተር ይሽሩን ዓለማየሁ አሳሰቡ።
በድጅታል ኢኮኖሚ ግንባታ የተመዘገቡ ለውጦችን በአገር አቀፍ ደረጃ በማስፋት በድጅታል ክህሎት የበለጸገና በድጅታል ኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ያረጋገጠ ማህበረሰብ ለመፍጠር የሚያስችል የሴቶችና የወጣቶች አገር አቀፍ የንቅናቄ መድረክ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው።
መድረኩን በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር የአይሲቲና የድጅታል ኢኮኖሚ ልማት ዘርፍ ሚንስትር ዲኤታ ይሽሩን ዓለማየሁ (ዶ/ር) በንግግር ከፍተውታል።
እንደ ዶክተር ይሽሩን በኢትዮጵያ በድጅታል ቴክኖሎጂ የበለጸገ እና በድጅታል ኢኮኖሚ የሚጠቀም ማህበረሰብ እንዲፈጠር አስቻይ ምቹ ሁኔታዎችን ተፈጥረዋል።
የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም መላ ህብረተሰቡን በማነቃነቅ በተለይም ሴቶች እና ወጣቶች ከዘርፉ እንዲጠቀሙ በየደረጃው ያሉ አደረጃጀት አመራሮች ሚናቸው የጎላ በመሆኑ ይህ የድጅታል ክህሎት ማበልጸጊያ ስልጠና መድረክ ተዘጋጅቷል ብለዋል።
ዶክተር ይሽሩን አክለውም ወጣቶች በተለይም አብዛኛው የህብረተሰባችን ክፍል የሆኑት ሴቶች ከድጅታል ቴክኖሎጂ በእጅጉ ተጠቃሚ ስለሚሆኑ የሚመለከታቸው ባለድርሻ እና አጋር አካላት በመቀናጀት በትኩረት መረባረብ ይጠበቅብናል ብለዋል።
በስልጠናው የድጅታል ክህሎትን በተለይም ከፋይናንሻል ቴክኖሎጂ አኳያ ስልጠናውን እየሰጡ ያሉትን የሚንስቴር መስሪያ ቤቱን እና የኢትዮ ቴሌኮምን ባለሙያዎች ያመሰገኑት ሚንስትር ደኤታው በተለይም የኢትዮጵያን ድጅታላይዜሽን ከመረጃ ቅብብሎሽና አውታረ ግንኙነት(Beyond Connectivity) ባሻገር አልሞ እየሰራ የሚገኘውን አንጋፋ ተቋምንና ለስልጠናው ድጋፍ ያደረጉ አካላትን ሁሉ በሴቶችና ወጣቶች ስም አመስግነዋል።
በስልጠናው አመራሮቹ ያገኙትን እውቀትና ክህሎት እስከታች በማውረድ የኃላፊነታቸውን በላቀ ትጋት እንዲወጡ ከአደራም ጭምር አሳስበዋል።
በስልጠናው ከመላ ኢትዮጵያ የተውጣጡ 120 የሚደርሱ የሴቶችና ወጣቶች አደረጃጀት አመራሮች ተሳትፈውበታል።
Most Viewed News
ትኩስ ዜና
41st Regular Council of Ministers Meeting Resolutions The council of ministers discussed and passed a decision on various issues at the 41st regular meeting today.
41st Regular Council of Ministers Meeting Resolutions The council of ministers discussed and passed a decision on various issues at the 41st ...
Read More5 Million Coders Professional Training
Register here to benefit from free online training opportunities through the Five Million Ethiopian Coders Initiative to develop basic coding ...
Read More5 million Ethiopian coders
The "5 million Ethiopian coders" initiative is a program that will help our youth to have the appropriate digital skills and create jobs and ...
Read MoreA delegation from Kagool,
A delegation from Kagool, a leading global data and analytics group, and Micro Tech London visited Ethiopia to assess opportunities in the ...
Read MoreA delegation led by the Minister of Innovation and Technology Dr. Belete Mola visited digital technology works in Bahirdar city.
A delegation led by the Minister of Innovation and Technology Dr. Belete Mola visited various institutions in Bahir Dar to digitalize their work ...
Read MoreThe government merged the former Ministry of Science and Technology and the Ministry of Communication and Information Technology to form the Ministry of Innovation and Technology in 2019.
Focus Areas
- Research
- Innovation
- Technology Transfer
- Digitalization
Contact
- Tell: +251118132191
- Email: contact@mint.gov.et
- Website: www.mint.gov.et
Connect to MInT