+251118132191
contact@mint.gov.et
የ "5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ" ኢኒሼቲቭ ወጣቶቻችን ተገቢው የዲጂታል ክህሎት እንዲኖራቸው በማድረግ ስራ እና ሀብትን በመፍጠር የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን በስፋት ለማቀጣጠል የሚረዳ ፕሮግራም ነው።ዶ/ር በለጠ ሞላ
አምሰት ሚሊዮን ዜጎች የዲጂታል ቴክኖሎጂ ስልጠና ተጠቃሚ የሚሆኑበት የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቪን
በዛሬው እለት በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ይፋ ሆኗል።
በመርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዶ/ር በለጠ ሞላ የ "5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ" ኢኒሼቲቭ ወጣቶቻችን ተገቢው የዲጂታል ክህሎት እንዲኖራቸው በማድረግ ስራ እና ሀብትን በመፍጠር የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን በስፋት ለማቀጣጠል የሚረዳ ፕሮግራም ነው ብለዋል።
ሚኒስትሩ ዛሬ፣ ቴክኖሎጂ የስራ መሳሪያ ብቻ ሳይሆን የለውጥ አራማጅ የሆነበት አዲስ የዘመን ምዕራፍ ላይ ደርሰናል ያሉት ሚኒስትሩ የነገዋን ኢትዮጵያ የሚቀርፁት የፈጠራ ባለሙያዎች እና ተመራማሪዎች ናቸው ብለዋል።።
የኢትዮ ኮደርስ ፕሮግራም ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን በዲጂታል ስነ ምህዳሩ ውስጥ በንቃት እንዲሳተፉ የሚያስችላቸውን ክህሎትና እውቀት በማስታጠቅ አዳዲስ እድሎች እንዲፈጠርላቸው እና ሀገራችን በቴክኖሎጂው መስክ ወደፊት እንድትገሰግስ በር የሚከፍት መሆኑንም ሚንስትሩ አንስተዋል።
የኢትዮኮደርስ ፕሮግራም ወጣቶቻችንን ለማብቃት፣ ፈጠራን ለማጎልበት እና የዲጂታል ዘመንን ግዙፍ አቅም ለመጠቀም መንግስት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ብለዋል።
የዲጂታል ኢትዮጵያን ለማረጋገጥ ወሳኝ ከሆኑት መሰረቶች አንዱ የዲጂታል ስነ ምህዳሩን መገንባት እና የዲጂታል ክህሎት በመሆኑ በዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ውስጥ ከኢኮኖሚው ለመጠቀም ሆነ አገልግሎት ለማቅረብ ወሳኝ መነሻ በመሆኑ የ 5 ሚሊየን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢኒሼቲቨ የወጣቶቻችንን የዲጂታል ክህሎት ለማሳደግ አንዱ ምላሽ ሆኖ መምጣቱን ተናግረዋል።
"ኮድ ማድረግ የኮድ መስመሮችን መጻፍ ብቻ አይደለም። ኮድ ማድረግ ችግር ፈቺ፣ ሂሳዊ አስተሳሰብ እና ፈጠራ ነው።"ያሉት ሚኒስትሩ ወጣቶቻችን የኮዲንግ ክህሎት እንዲኖራቸው ስናደርግ ሰፊ ወደ ሆነው የዲጂታል አለም በልበ ሙሉነት በመቀላቀል ሌሎች የፈጠሩዋቸውን አፕሊኪሽኖች መጠቀምም ብቻ ሳይሆን በቀጣይ አገርን የሚጠቅም እና የሰው ልጆችን ህይወት የሚያቀሉ በርካታ አፕሊኪሽኖችን በራሳቸው ማልማት እንዲችሉ መንገዱ እየተመቻቸላቸው እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል ብለዋል።
Most Viewed News
The government merged the former Ministry of Science and Technology and the Ministry of Communication and Information Technology to form the Ministry of Innovation and Technology in 2019.
Focus Areas
- Research
- Innovation
- Technology Transfer
- Digitalization
Contact
- Tell: +251118132191
- Email: contact@mint.gov.et
- Website: www.mint.gov.et
Connect to MInT