+251118132191
contact@mint.gov.et
በሀገራችንን የሳይንስና ቴክኖሎጂ መረጃ መዳረሻ ማዕከላትን በመገንባት ለሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገት ልንጠቀምበት እንደሚገባ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ገለፁ፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኮሪያ ሪፐብሊክ ብሔራዊ የመረጃ ማህበረሰብ ኤጀንሲ ጋር በመተባበር የመረጃ መዳረሻ ማዕከል (Information Access Center) ለመገንባት የሚያስችል ምዕራፍ ላይ ምክክር አካሂደዋል፡፡
ዓላማውም የሀገሪቱን የቴክኖሎጂ መረጃ ልማት ለማሳካትና ተገቢ የሳይንስና ቴክኖሎጂ መረጃዎችን ለሚመለከታቸው አካላት በተቀላጠፈ ደረጃ ተደራሽ ለማድረግ ያለመ ነው፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚውን የሚያሳልጥ ህዝቡ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እንዲለማመድ እድል ለመስጠት በህዝብና በመንግስት ተቋማት እና በአገር አቀፍ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የቅርብ ጊዜውን የአይሲቲ አገልግሎት የታጠቁ መረጃዎችን ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል ማዕከላትን ለማቋቋም ከአጋር አካላት ጋር በትብብር እየሰራ ነው ብለዋል፡፡
የሀገራችንን የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ መረጃ ልማትን በማጎልበት የዘርፉን የኢኮኖሚ ምዕራፍ ለማሸጋገር ማዕከሉ ትልቅ ሚና እንዳለው ገልፀዋል፡፡
ለአንድ ሀገር የተደራጀ መረጃ ከወርቅ በላይ የሆነ ሀብት ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ሀገራችን ያላትን መረጃ በማዕከላት በማደራጀት በተለይም ለምርምር ዘርፉ ምቹ ስነምህዳር ለመፍጠር፣ ያለውን አስተዋፅዖ ለመጠቀምና የዲጂታል ኢኮኖሚውን ለማጎልበት ሁሉም ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
የኮሪያ ሪፐብሊክ ብሔራዊ የመረጃ ማህበረሰብ ኤጀንሲ ልካን መሪ ዮን ጆንግ የመረጃ ተደራሽነት ማዕከል (Information Access Center) ፕሮጀክት ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር ከሚሰሩ ስራዎች ውስጥ የሳይንስና ቴክኖሎጂ መረጃ መዳረሻ ማዕከላትን በሚፈለገው መልኩ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
እያንዳንዱ ማዕከል የአይሲቲ ውስብስብ ክፍል፣ የአይሲቲ ማሰልጠኛ ክፍል፣ የሴሚናር ክፍል እና የይዘት ማምረቻ ክፍል እንደሚኖረውም ተጠቁሟል፡፡
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች