+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ኢትዮጵያ ለአፍሪካ አባል ሀገራት በኒኩለር ኢንጂነሪግ የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም እንድትሰጥ በአለም አቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ (IAEA) ተመረጠች።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ አለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ (IAEA)፣ በቻይና መንግስት የ Tsingua University፣ ኦንዲሁም የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ (AASTU) ባደረጉት የተለያየ ጊዜ የምክክር መድረክ ለሀገር ውስጥና ለአፍሪካ አባል ሀገራት በኢትዮጵያ የኒኩለር ሳይንስና ቴክኖሎጂ የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም እንዲሰጥ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

ስምምነቱ በኢትዮጵያ የኑክሌር ሳይንስና ቴክኖሎጂ የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም በመክፈት ፤ በኢትዮጵያ የኑክሌር ሳይንስና ምርምርን በማስፋትና በዘርፉም ኢትዮጵያዊ ኢንጂነሮችን በማፎራት ብሎም ለአፍሪካ አባል ሀገራት የትምህርትና ስልጠና ማዕከል እንዲሆን በማሰብ በኢንዱስትሪ፣ በጤና፣ በግብርና፣ በአካባቢ ሳይንስ፣ በማዕድን፣ በማኑፋክቸሪንግና በሌሎችም ዘርፎች ላይ አቅም በመፍጠር ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ያለመ ነው ተብሏል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ሀገራችን እያከናወነች ያለውን የኢኮኖሚ እድገት ለማሳለጥ በኒኩለር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ብቁ ዜጋን መፍጠር ወሳኝ ሚና እንዳለው ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ የአፍሪካ መግቢያ በር ናት ያሉት ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የኒኩለር ሳይንስና ቴክኖሎጂ የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ለአፍሪካ IAEA አባል ሀገራት እንዲሰጥ ኢትዮጵያ የተመረጠችው ዘርፈ ብዙ ድርድሮች ተደርገውና የማስተናገድና አቅሟ ከግምት ውስጥ ገብቶ እንደሆ ገልፀዋል፡፡

ሀገራችን የኒኩለር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፉን ለሰላማዊ ህልውና ኢኮኖሚ ማበልፀጊያነት ለመጠቀም በሰው ሀይል ልማት ላይ በመስራትና ከፖሊሲዎቻችን ጋር በማናበብ ዘርፉን ለሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገት ለመጠቀም በትብብር አውድ ላይ በትኩረት እየሰራች ነው ብለዋል፡፡

የአለም አቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ የቴክኒክ ትብብር ም/ዋና ዳይሬክተር Hua Liu ለአፍሪካ አባል ሀገራት በኢትዮጵያ የኒኩለር ሳይንስና ቴክኖሎጂ የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም መሰጠቱ ኢኮሚውን ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ከአሁን ቀደም ከሚኒስትሩ ጋር ባደረጓቸው ተከታታይ ውይይቶች የገለጹት ነበር።

አክለውም በኢትዮጵያ የኑኩሌር ሳይንስና ቴክኖሎጂ የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ለመስጠት የሚያስችሉ ላብራቶሪና አስፈላጊ ግብዓቶች በአለም አቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲና በቻይና መንግስት በኩል ድጋፍ እንደሚደረግ መግባባት ላይ ተደርሷል።

በዘርፉ የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራሙን ለመስጠት የአዲስ አበባ የሳይንስና ቴክኖለጂ ዩኒቨርስቲና የቻይና Tsinghua ዩኒቨርስቲ በጋራ በመስራት እስከ 10 የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን ለ6 ወር በቻይና Tsinghua ዩኒቨርስቲ ሰልጥነው በሀገራች ለአፍሪካ IAEA አባል ሀገራት በኢትዮጵያ የኒኩለር ሳይንስና ቴክኖሎጂ የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም እንደሚሰጡ ተገልጿል፡፡

በመጨረሻም በቀጣይ ወደስራ የሚያስገባ የሶስትዮሽ የስምምነት ሰነድ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ በአለም አቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲና በቻይና መንግስት ለመፈራረም የሚያስችል የጋራ አቅጣጫ ተወስዷል፡፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ