+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ኢትዮጵያ አለም የደረሰችበት ምዕራፍ ላይ እንድትደርስ በቴክኖሎጂ የዘመኑ ተቋማትን መገንባት ግዴታ መሆኑን ዶ/ር ይሹሩን ዓለማየሁ ገለፁ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ጋር በጋራ ለመስራት በሚያስችሏቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

ምክክሩ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎትን በቴክኖሎጂ በማዘመን የዲጂታል አሰራር ስርዓትን ለማጎልበት ያለመ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሹሩን አለማየሁ (ፒ ኤች ዲ) ኢትዮጵያ ዓለም የደረሰበት የቴክኖሎጂ ምዕራፍ ላይ ለመድረስ የምታደርገውን ጥረት ለማሳካት ተቋማት ጊዜውን የዋጀ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ሊያረጋግጡ ይገባል ብለዋል፡፡

ለተቋም እድገት የተክኖሎጂው ሚና የላቀ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴታው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ስራዎችን ለማዘመንና ዓለም የደረሰበት የቴክኖሎጂ ምዕራፍ ላይ ለመድረስ በጋራ ያለንን አቅም አሟጠን በመጠቀም ሀገራችን የምትሻውን ውጤት ለማስመዝገብ ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

ተቋሙ ያለውን የአሰራር ስርዓት ዲጂታላይዝ በማድረግና በማዘመን ሀገራችን ለዘርፉ የምታወጣውን ከፍተኛ ወጪ ከማስቀረት ባሻገር ዜጎች መረጃዎቻቸውን ባሉበት ሆነው እንዲያገኙ በማስቻል ጉልበታቸውን፣ ሀብታቸው እንዲቆጥቡ ለማስቻል ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው ተቋሙን ከጎበኙ በኃላ ከፍተኛ ጫና ያለበት ተቋም በመሆኑ ችግሩን ለመቅረፍ አስፈላጊ እርምጃዎች በአፋጣኝ እንዲወሰዱ እና ወደ ስራ እንዲገባም አሳስበዋል፡፡

የትምህረት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ ተቋሙን ለማዘመንና አለም የደረሰበትን ቴክኖሎጂ ለመጠቀም ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

አክለውም በተለይ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር የሚሰሩ ስራዎች ለተቋሙ እጅግ አስፈላጊ ስለሆኑ በቅርበት በመምከር በራሳችን ቴክኖሎጂ በመስራት የሀገራችንን የዲጂታል ሉዓላዊነት ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል፡፡

ሁለቱም ተቋማት በጋራ በመምከር በፖሊሲ፣ በሮድማፕና በኢንፍራስትራክቸር ላይ በጋራ ለመስራት የጋራ ኮሚቴ ያቋቋሙ ሲሆን ስራዎች ቀጣይነት እንዲኖራቸውና የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት የስምምነት ሰነድ እንደሚፈራረሙም ተጠቁሟል፡፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ