+251118132191
contact@mint.gov.et
የአለም የኢኮኖሚ ግስጋሴ መዘወሪያ የሆነውን የቴክኖሎጂ እውቀትን በመታጠቅ ቀጣይነት ያለው የሀገራችንን ሁለንተናዊ እድገት ልናረጋግጥ ይገባል ዶ/ር ባይሳ በዳዳ፡፡
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ የጎለበተ እውቀት የታጠቁ ሰራተኞችን ለማፍራት በየጊዜው መሰልጠን፣ ማወቅና መተግበር በሚያስችል አውድ ውስጥ ለመጓዝ ሁሉንም ሰራተኞች ያሳተፈ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲው ስልጠናዊ ምክክር አካሂዷል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ኢትዮጵያ የአለም ኢኮኖሚ አካል ለመሆን በቴክኖሎጂ ዘርፍ ላይ ያላትን እውቀት ማጎልበትና መጠቀም ፍላጎቷ ብቻ ሳይሆን ግዴታም ጭምር መሆኑን ተገንዝቦ ሁሉም በያለበት የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያደጉ ሀገራት ኢኮኖሚ መሰረት ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው የሀገራችንን የቴክኖሎጂ ፍላጎቶችና ችግሮች ለመፍታት ሀገራዊ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ፖሊሲው ያስቀመጣቸውን አጀንዳዎች በመተግበር የሚፈለገውን የኢኮኖሚ እንድገት ማምጣት እንደሚያስችል ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ ዘመኑን በመረዳት በዘርፉ ላይ በትኩረት እየሰራች ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ሀገራችን እምቅ ሀብትና ሰፊ ወጣት ሀይል ያላት ሀገር ስለሆነች ዘርፉን ለማሳካትና ለማሳደግ የተፈጠሩት መልካም ስነምህዳሮች በመጠቀም በዲጂታልና በፈጠራ ስራ ላይ አሁን ካለችበት ደረጃ በእጥፍና በፍጥነት ለመጓዝ ሁሉም ሊተጋ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታው የፖሊሲው አቅጣጫዎችና ስትራቴጂዎች በሆኑት በሰው ሀብት ልማት፣ በቴክኖሎጂ ልማት፣ ሽግግር እና የእዉቀት አስተዳደር፣ በምርምርና ልማት፣ በኢኖቬሽን እና የኢንተርፕራይዞች ተወዳዳሪነት፣ በፋይናንስ አቅርቦት፣ መዋዕለ-ንዋይ፣ ድጋፍና ማበረታቻ፣ በጥራትና አዕምሯዊ ንብረት፣ በትብብር እና ትስስር፣ በአካባቢያዊ፣ ማህበራዊና ባህላዊ ልማት ላይ ማብራሪያ በመስጠትም አስገንዝበዋል፡፡
በእውቀት መጋራቱ ላይ የተሳተፉት ሰራተኞች ቀጣይነት ያላቸው እንዲህ ያሉ መድረኮች ለስራዎችቸው ውጤት ማስመዝገብ ሚናቸው የላቀ እንደሆነና የቴክኖሎጂ እውቀት ለመታጠቅ የተገኘውን እድል እንደሚጠቀሙና ወደ ውጤት እንደሚቀይሩም ገልፀዋል፡፡
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች