+251118132191
contact@mint.gov.et
የአዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከዋና መስርያ ቤት እስከ ወረዳ የሚገኙ 367 ባለሙያዎች የ5 ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ወስደው ማጠናቀቃቸውን አስታወቀ።
ኤጄንሲው በዛሬው እለት ስልጠናቸውን ላጠናቀቁ 127 ባለሞያዎች የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሽሩን አለማየሁ እና በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ-አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ በተገኙበት እውቅና ሰጥቷል።
በዝግጅቱ ላይ ኤጀንሲው የተቀመጠውን ሃገራዊ አቅጣጫ በተደራጀ መልኩ መምራቱን ያመሰገኑት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ዶ/ር ይሽሩን አለማየሁ ሌሎች ክልሎች እንደ ሃገር የአዲስ አበባ ከተማ አርዓያነት ሊከተሉ እንደሚገባ አንስተዋል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ-አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ የስልጠናው ዋና ግብ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚችል ብቁ ሰራተኛ መፍጠር መሆኑ ታውቆ ሰልጣኞች ክህሎቱን ወደ ተግባር እንዲቀይሩ አፅንዖት ሰጥተዋል።
ባሉበት ሆነው በነፃ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ፣ በዳታ ሳይንስ ፣ በዌብ ፕሮግራሚንግ እና በአንድሮይድ ማበልፀግ ዙርያ የተዘጋጁ ነፃ የኦንላይን ስልጠናዎችን ለመውሰይ በ https://ethiocoders.et/ ላይ ይመዝገቡ።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች