+251118132191
contact@mint.gov.et
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለስታርታፕ ስነምዳር ግንባታ በሚውል የአለም አቀፍ ድጋፍ ረገድ ምክክር ተደረገ፤
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ እና የፈረንሳይ ዴቨሎፕመንት ኤጀንሲ የኢትዮጵያ ዳሬክተር ሚስተር ሉዊስ አንቶኒ ጋር በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ስታርትአፕ ሥነ-ምህዳር ለማጠንከር ወሳኝ የሆኑ የድጋፍ መስኮችን በተመለከተ ፍሬያማ ውይይት ተካሄዷል።
በዚህም የስታርታፕ አዋጁና ተያያዥ ጉዳዮቸን በተመለከተ፤ በቀጣይ የኢተዮጵያ ስታርታፖች በፈረንሳይ አለምአቀፍ የስታርታፕ ሁነት ላይ ስለሚኖራቸው ተሳትፎ እንዲሁም ሚንስቴር መስሪያቤቱ በስታርታፕ ዙሪያ ባከናወናቸው ተግባራት ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡
ከሚንስቴር መስሪያቤቱ የተደረገውን ውይይት ተከተሎ፤ የፈረንሳይ ዴቨሎፕመንት ኤጀንሲ ከአውሮፓ ህብረት እና ኤክስፐርቲስ ፍራንስ ጋር በመተባበር የስታርትአፕ ሥነ-ምህዳሩን ለማጠናከር 10 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ለማድረግ እየተዘጋጀ መሆኑን አስታውቋል።
ይህም ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረውንና በቅርቡ ወደስራ የሚገባውን የስታርትአፕ አዋጅ ወደ ተግባር ለማሸጋገር ይረዳል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የ ስታርትአፕ ኢንኩቤሽን ሞዴሎችን ማሻሻል እና የስታርትፖች አቅም ማጠንከር የፈንድ ምንጮችን መጨመር እና ማባዛት ላይ ሰፊ ውይይት እና መግባባት ላይ የተደረሰ ሲሆን በቀጣይም በተጠናከረ መንገድ የሚሰራ መሆኑን በውይይት ወቅት ተመላክቷል፡፡
በመጨረሻም በኢትዮጵያ ያሉ ስታርትአፖች በአውሮፓና ፈረንሳይ የስታርታፕ ስነምህዳር እንቀስቃሴዎች ረገድ ተሳትፎ የሚያደርጉብት ዕድል በሚፈጠርብት ሁኔታ ስራዎች አስመልክቶ ክቡር ዶ/ር ባይሳ በዳዳ እና ሚስተር ሉዊስ አንቶኒ በቀጣይ በጋራ የሚሰሩ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች