+251118132191
contact@mint.gov.et
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከቪዛ ዓለም አቀፍ አገልግሎት ጋር በጋራ ለመስራት ተስማሙ።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከቪዛ ዓለም አቀፍ አገልግሎት ጋር በሀዋላ፣ በዲጂታል ፋይናንስና በአዳዲስ የትብብር ዕድሎች ላይ በጋራ ለመስራት መክረዋል።
ምክከሩ በዓለም አቀፍ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶች ላይ አዳዲስ የትብብር ዕድሎችን በመፍጠር የዲጂታል ኢኮኖሚውን አቅም ለማጎልበት ያለመ ነው።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሹሩን ዓለማየሁ የኢትዮጵያ መንግስት በእኩልነትና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ የዲጂታላይዜሽን ትብብር እንዲጎለብት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው ገልፀዋል።
የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስኬት ለማረጋገጥ በህግ ማዕቀፍ፣ በመሠረተ ልማቶችና በሰው ሀይል ግንባታ ላይ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ሀገራዊ ስራዎችን ዲጂታላይዝ ለማድረግና የፋይናንሺያል ምርቶችንና አዳዲስ አገልግሎቶችን በኢትዮጵያ ለማዳረስ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።
የቪዛ ኢንክ የደቡብና ምስራቅ አፍሪካ ሪጅን ም/ፕሬዝዳንት ሚካኤል በርነር ዓለም አቀፍ የቪዛ አገልግሎትን በኢትዮጵያና በቀጣናው ሀገራት ተደራሽ ለማድረግ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል።
የቪዛ ክፍያ መፍትሄዎችን፣ ቴክኖሎጂዎችንና የዲጂታል ስነ-ምህዳርን በኢትዮጵያ ለማጎልበት ያስችላል ያሉት ም/ፕሬዝዳንቱ ዓለም አቀፍ እና ክልላዊ ምርጥ ተሞክሮዎችን ተግባራዊ እንደሚያደርጉም ተናግረዋል።
የመንግስት አገልግሎቶችን ዲጂታይዝ ለማድረግ፣ የፋይናንስ አካታችነትን ለማሳደግ፣ የገቢ አሰባሰብ ቅልጥፍናን ለማሻሻል እና የኢትዮጵያን አጠቃላይ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን አጀንዳ ፣ የዲጂታል ስትራቴጂው የቅድሚያ ፕሮጀክቶችን እና የትግበራ እቅዶችን ለመደገፍና በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ተደርሷል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች