+251118132191
contact@mint.gov.et
የአእምሯዊ ንብረት እና የቅጅ መብት ስራዎችን ለማስጠበቅ ተግባራዊ እየተደረገ ያለው ህጋዊ አሰራር በተቀናጀ መልኩ ተግባራዊ እየተደረገ ነው ዶ/ር ባይሳ በዳዳ
በኢትዮጵያ ለ23ኛ ግዜ የሚከበረው የዓለም አቀፍ የአእምሯዊ ንብረት ቀን ''ሙዚቃና አእምሯዊ ንብረት፤ ፈጠራን ማጎልበት/ማፍጠን'' በል መሪ ቃል በተለያዩ መርሀ ግብሮች እየተከበረ ይገኛል።
ዝግጅቱ የከፈቱት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ የቴክኖሎጂ እድገትን ለማረጋገጥ የፈጠራ ስራ ትልቁን ድርሻ እንደሚወስድ ተናግረዋል።
የአእምሯዊ ንብረት እና የቅጅ መብት ስራዎችን ለማስጠበቅ ተግባራዊ እየተደረገ ያለው ህጋዊ አሰራር በተቀናጀ መልኩ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትር ድኤታው የፈጠራ ባለሙያዎች ፈጠራዎቻቸውን የማስመዝገብ ልምድን ሊያዳብሩ እንደሚገባ ገልጸዋል ።
አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችና የፈጠራ ስራዎች ለሀገር ልማትና ለዜጎች አብሮነት የድርሻቸውን እንዲወጡ በማድረግ በኩል በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸው፤ የመብት ማስጠበቅ ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባልም ብለዋል።
የፈጠራ ስራ ውጤቶችን በአግባቡ ጥቅም ላይ በማዋል ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታውን ለማጉላት በትኩረት እየተሰራ ስለመሆኑም ሚኒስትር ዴኤታው አብራርተዋል።
እለቱን አስመልክቶ የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ወልዱ ይመስል እንደገለፁት የፈጠራ ስራ ውጤቶች ለሀገር ገፅታ ግንባታ፣ ለስራ እድል ፈጠራና ለቴክኖሎጂ መስፋፋት ጉልህ አስተዋጽኦ አላቸው።
ከፈጠራ ስራ ዘርፎች መካከል የሙዚቃ ፈጠራ ስራ በሁሉም መስክ ለሚከናወኑ ተግባራት አጋዥ መሳሪያ ስለመሆኑም አንስተዋል።
ኢትዮጵያ ብዙ ባህል፣ እሴትና ትውፊት ያላት ሀገር መሆኗ ደግሞ ለሙዚቃ ፈጠራ ስራ መጎልበት ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ነው።
መንግስት የሙዚቃና መሠል የፈጠራ ስራዎች እንዲጠበቁና ለሀገር ያላቸውን ፋይዳ ይበልጥ እንዲያጎሉ የሚያስችሉ የአሰራር ስርዓቶች እየዘረጋ መሆኑንም አብራርተዋል።
በዚህ ረገድ ባለስልጣኑ የሀገራትን ተሞክሮ በመቀመር፣ ከዘርፉ ተዋንያን ጋር ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከርና የምዝገባና መሰል አሰራሮችን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ማድረግ ከተከናወኑ ተግባራት መካከል ተጠቃሽ ናቸው።
የፈጠራ ስራን ከማበረታታት በዘለለ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታውን ለማጉላት ምቹ እድልን እየፈጠረ ይገኛል።
ለአብነትም ባለፈው አንድ አመት ብቻ ከ5 ሺህ በላይ የምዝገባና የጥበቃ ስራ ማከናወን ማቻሉን ገልጸው በዘንድሮው አመትም ወደ 7 ሺህ 5 መቶ ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ይህም ዘርፉን ይበልጥ ለማዘመን፣ ተደራሽነቱን ለማስፋትና የፈጠራ ስራ ባለሙያዎች ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ምቹ ሁኔታን እየፈጠረ መሆኑን አክለዋል።
በሳይንስ ሙዝየም ለሁለት ቀናት በመካሄድ ላይ በሚገኘው መርሃ ግብሩ ላይ የፈጠራ ውጤቶች አውደ ርዕይ የተከፈተ ሲሆን የበዓሉ ተሳታፊዎችና ተጋባዥ እንግዶች አውደ ርዕዩን ጎብኝተዋል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች