+251118132191
contact@mint.gov.et
ሀገራችን የለውጥ ሃይል ፣ የግንኙነት መረብና የእድገት ሞተር በሆነው ኢንተርኔት ላይ በትኩረት እየሰራች መሆኑን ዶ/ር በለጠ ሞላ ገለፁ።
ሁለተኛው ብሔራዊ የበይነ-መረብ አስተዳደር ጉባኤ ፣ የትምህርት እና የምርምር፣ የመንግስት ተቋማት ፣ የሲቪል ማህበራት፣የግሉ ዘርፍ ተወካዮች፣ባለድርሻዎች እና ወጣቶች በተገኙበት "ለወደፊቷ ዲጂታል ኢትዮጵያ የብዙኀን ባለድርሻ አካላት ትብብር " (Multi-Stakeholder Collaboration for Ethiopia's Digital Future) በሚል መሪ ቃል ጉባኤው ተካሂዷል።
በጉባኤው ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ሀገራችን ባለፉት 4 አመታት በአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ እና በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ማዕቀፎች ላይ የዲጂታል ልማቱን ለማሳካት በርካታ ስራዎችን ማከናወኗን ገልፀዋል።
ሀገራችን በዲጂታል ኢኮኖሚ እድገት ላይ የምናልመው ውጤት እንዲመጣ የግሉ ዘርፍ ዳታ ማዕከላትን በማስፋፋትና አዳዲስ የዲጂታል አገልግሎቶችን በማሳለጥ በከፍተኛ ደረጃ የበኩሉን አስተዋፅዖ እያደረገ መሆኑን አንስተዋል።
አካታች ዲጂታል ኢኮኖሚን ለማረጋገጥ የዲጂታል እውቀት ያለውን ወሳኝ ድርሻ በመረዳት መንግስት በተለይ የ 5ሚሊዮን ኮደሮች ፕሮግራም በመንደፍ ተግባራዊ ማድረጉ ኢትዮጵያን በአለምአቀፍ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ካርታ ላይ ለማስቀመጥ ሚናው ከፍተኛ ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ አማካሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ተሾመ ወርቁ በዓለም ዙሪያ ያሉ ግለሰቦችን የንግድ ድርጅቶችን እና መንግስታትን የማገናኘት ሀይል ያለው በይነ መረብ ላይ ጥንቃቄና መተባበርን የሚሹ ፈተናዎች በጋራ መሰራት አለበት ብለዋል።
ጉባኤው ለኢትዮጵያ ዲጂታል ሰነምህዳር እድገት ወሳኝ በሆነው አሳታፊ የበይነ መረብ አስተዳደር ጉዳዮች ላይ የጋራ የሆነ ውጤት ለማምጣት ያለመ መሆኑን ገልፀዋል።
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የዳበረ ዲጂታል ስነ-ምህዳር ለመፍጠር ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር የሚያደርገውን ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተጠቁሟል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች