+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ሀገራችን የያዘችውን የኢኮኖሚ ዕድገት ጉዞ ለማስቀጠል ቴክኖሎጂ ከፍተኛ ድርሻ አለው። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አመራሮችና ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የ2016 በጀት አመት ዕቅድ አፈፃፀም እና በ2017 በጀት አመት ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል።

በውይይቱም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጆ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ መንግስት የሰጠንን ሀገራዊ ሀላፊነት ለመወጣት የሀገራችንን የኢኮኖሚ ጉዞ በቴክኖሎጂና በዲጂታላይዜሽን እንዲደገፍ ማድረግ አለብን ብሏል።

ስትራይድ ኢትዮጵያን አጠናክረን በማስቀጠል ወጣቶች በውስጣቸው ያለውን እምቅ ሀብት እንዲያወጡ መስራት አለብን ያሉት ክቡር ሚኒስትሩ በ2016 በጀት አመት የሰራናቸው የስታርትአፕ እና የምርምር ድጋፍ ስራዎች አጠናክረን በማስቀጠል ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ብቻ ሳይሆን ቴክኖሎጂ አምራች ሀይልም መፍጠር ይጠበቅብናል ብለዋል።

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ከኮርያ መንግስት ጋር በመተባበር በኢኖቤዝ ኬ ኢትዮጵያ በስታርትአፕ ዙርያ ለወጣቶች የተሰጠውን ስልጠና እና የሚደረገውን ድጋፍ

እንደ ሃገር በዘርፉ ውጤት ማስመዝገብ የቻለ እንደሆነ ተጠቅሷል።

በሀገራዊ የኢኖቬሽን፣ ቴክኖሎጂና ምርምር ዘርፍ በኩል 95 የምርመር ተቋማት ተለይተው በተለያዩ ዘርፍ የሚደረጉ ሀገራዊ ምርምሮችን የመደገፍ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ተነስቷል።

ወጣቶች በስታርትአፕ ስነምህዳር ተሳታፊ ለማድረግ ስትራይድ ኢትዮጵያ ኤክስፖ 2024፣ ስታርትአፕ ኢትዮጵያና መሰል ሀገራዊ መድረኮችን በማዘጋጀት ወጣቶች የመደገፍና የማበረታታት ስራ መሰራቱም ተነስቷል።

የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፉን በተጠናከረ መንገድ ለመምራት የአሰራር ስርአት ከመዘርጋት አንጻር በርካታ ስራዎች የተሰሩ ሲሆን የግል ዳታ ጥበቃ አዋጅ መጽደቅ ተጠቃሽ መሆኑ ተነስቷል።

ግንዛቤን ከማሳደግ አንጻር በአመቱ ለ82 የፌደራልና የክልል ተቋማት በወረዳ ኔት፣ በሳይበር ሴኩሪቲ፣ በዲጂታል ቅጅ ወዘተ ስልጠናዎች መሰጠቱ ተገልጿል።

በቴክኖሎጂ የተደገፈ የመንግስትና የንግድ አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል ከሚሰሩ ስራዎች አንዱ የሆነው የመንግስት የቢዝነስ ፖርታል ላይ በአራት ከተሞች መተግበሩ ለ431 የአይሲቲ እና ዲጂታል የንግድ ተቋማት የብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ መሰጠቱ በግምገማ መድረኩ ተጠቁሟል።

በቀጣይ በኢኖቬሽንና ምርምር ልማት፣በዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ፤ስታርታፖችን ከማበረታታትና ከመደገፍ አንጻር በትኩረት እንደሚሰራ ተገልጿል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ