+251118132191
contact@mint.gov.et
ሀገራችን የጀመረችውን የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ እውን ለማድረግ ዘርፈብዙ ስራወችን በአስደናቂ ውጤት እየመራ የሚገኘው ኢትዮ ቴሌኮም ሊመሰገን ይገባል። ዶ/ር በለጠ ሞላ
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች የኢትዮ ቴሌኮምን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ባለፉት ጥቂት አመታት በሀገራችን የዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት የጀመርነው ስራ እውን ለማድረግ የተለያዩ ተቋማት የሚያደርጉት እንቅስቃሴ የሚበረታታ ሲሆን ኢትዮ ቴሌኮም ከፊት ሆኖ እየሰራው ያለው ስራ ቀዳሚ ሚና አለው ብለዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም ከሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ አንፃር በመሰረተ ልማት ዝርጋታ እና በኢንተርኔት አቅርቦት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው በመቀጠል ዜጎች የኑሮ ዘዴያቸውን ቀላል በማድረግና የኢኮኖሚ አቅማቸውን በመገንባት ትልቅ ሚና መጫወት እንዳለበት አንስተዋል።
ይሀንን እውን ለማድረግም የሚያስችሉ ፖሊሲዎችን፣ ስትራቴጂያችንንና ሌሎች የአሰራር ስርዓቶችን በመዘርጋት ሚኒስቴር መስሪያቤቱ አብሮ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ክብርት ፍሬሕይወት ታምሩ ኢትዮ ቴሌኮም ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ እየሰራቸው ያሉ ስራዎችን አብራርተው ስራዎችን ወደላቀ ግብ ለማድረስ በቅንጅት መስራትን የሚጠይቅ መሆኑን አብራርተው ይህንን ቅንጅት እየፈጠርን እንሰራለን ብለዋል።
የጀመርነውን የዲጂታል ጉዞ እውን ለማድረግ በምናደርገው እንቅስቃሴ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ቀርፆ እየሰራቸው ያሉ ስራዎችን የሚደነቅ ነው ያሉት ወ/ሪት ፍሬሕይወት ጉዟችን ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ በመሆኑ የዲጂታል የፋይናንስ ስርአታችንን እና ሌሎች የዲጂታል አገልግሎቶቻችንን ለማዘመን ሲባል በገጠራማ የሀገራችን አከባቢዎች የ3G እና በአብዛኛው የሀገራችን ክፍሎች የ4 እንዲሁም የ5G የኢንተርኔት አገልግሎት ማስፋፋት ላይ በስፋት እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።
ከተጎበኙት የኢትዮ ቴሌኮም ስራዎች ውስጥ በአድዋ ሙዝየም የተገነባው Experience Center የኢትዮቴሌኮም ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ 130 እድሜ በላይ ማስቆጠሩን እና እስካሁን ያለውን የቴክኖሎጂ ሽግግር ሂደት የሚያሳይ፣ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ከ2G ጀምሮ እስከ 5G የኢንተርኔት አገልግሎት ማስፋፋት ላይ ያደረገውን ጉዞ፣ የ5G ኢንተርኔት አገልግሎት ምንነት፣ ተቋማት ከወረቀት ስራ ሊያስወጡ የሚችሉ ስማርት ኦፊስና በስማርት ሆም የተሰሩ ስራዎች የተጎበኙ ሲሆን በተለይም የዲጂታል ኢትዮጵያ ትግበራ በፋይናንስና ክፍያ ስርአት፣ በግብርና፣ በጤና፣ በስማርት ከተማ፣ በትምህርት፣ በቱሪዝም፣ በማይኒንግና በልዩልዩ ዘርፎች ሊያመጣ የሚችለው ውጤት ሾውኬዝ የተደረገበት ነው።
በቴክኖሎጂ የተደገፈ የማዕድን ማውጫ ስርዓት፣ የግብርናውን ስራ ለማዘመን የሚያስችል ዘመናዊ የግብርና ስርዓት፣ ከተሞቻችንን በቴክኖሎጂ የተደገፋ እንዲሆኑ የሚያደርግ ዘመናዊ ከተማ እንዲሁም የክፍያ ስርዓት ዲጂታላይዝ የሚያደርጉ አሰራሮች መሰራታቸው አሳይተዋል።
በመጨረሸም ለዲጂታል ኢትዮጵያ ስኬት በሙሉ አቅም አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ሰፊ አቅም ያላቸው ዳታ ሴንተሮች መገንባታቸውና በዚህ ዳታ ሴንተር እስካሁን የተለያዩ ሴክተሮች እና 18 ባንኮች ዳታቸውን እያስቀመጡ መሆኑ የተመላከተ ሲሆን ዳታ ሴንተሮች ደህንነት ጠንካራ እንዲሆኑ ትልቅ ስራ ተሰርቷል ብለዋል። አጠቃላይ የስራ ጉብኝቱ ውጤታማ ሲሆን በተለይ ለተሻለ ውጤታማነት ሁለቱ ተቋማት በቅንጅት የሚሰሯቸውን ስራወች ለመለየት ያስቻለ በመሆኑ የጋራ መድረክ በመፍጠር በየግዜው ስራወችን እየገመገሙ እንደሚሰሩ ተገልጿል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች