+251118132191
contact@mint.gov.et
ሀገራዊ ህልማችንን ዕውን ለማድረግ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዛችንን በማፋጠን በአገልጋይነት መንፈስ መስራትና መምራት ይጠበቅብናል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሽሩን አለማየሁ፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የአይሲቲና ዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ከዘርፉ የስራ ሀላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር በተያዘው በጀት አመት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የሚያስችል የምክክር መድረክ አካሄዱ፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሽሩን ሀገራችን የዲጂታል ኢኮኖሚ እድገት ለማበልፀግ በዘርፉ ላይ ያሉ ተዋናዮች ጊዜያቸውንና ጉልበታቸውን መሰዋት በማድረግ የተያዙትን እቅዶች በመናበብና በመደጋገፍ ማሳካት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ሀገራችን ከእኛ ብዙ ትጠብቃለች ያሉት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ዘርፉን በማበልፀግ የአገልጋይነት ሚናችንን በመወጣት በማህበረሰባችን ውስጥ ያሉ ችግሮችን መፍታት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
በዘርፉ ላይ የምንሰራቸውን ስራዎች በእቅድ መምራት ከቻልን በእያንዳንዱ እንቅስቃሴያችን ተጨባጭ ለውጥና ሊመዘገብ የሚችል ውጤት ማምጣት በቀላሉ እንሚቻልም አስገንዝበዋል፡፡
ዘርፉ በየጊዜው በፍጥነት እያደገና ውስብስብ እየሆነ ስለመጣ አስፈላጊ የሆኑ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች ከማግኘትም ባለፈ ሁሉም እራሱን ለማብቃት ጥረት ማድረግ እንደሚጠበቅበት ገልፀዋል፡፡
በምክክሩ ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የተሰጠ ሲሆን ስራዎች ይበልጥ ለማሳለጥ በየወሩ የጋራ የሆነ ግኑኝነት በመፍጠር የሚያጋጥሙ ክፍተቶችን በመሙላት ለተሻለ ውጤትና በጋራ ለመስራት ቀጣይነት ያለው መድረክ ወሳኝ ሚና እንዳለው ተሳታፊዎች ጠቁመዋል፡፡
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች