+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ሀገራዊ ለውጡ ያስገኛቸው ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ እድገት ስኬታማነታቸው በተግባር የተረጋገጠ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ገለፁ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት ሠራተኞች ለውጡን ተከትሎ ባለፉት 7 ዓመታት በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍና በሌሎች የሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገት ላይ የመጡ ለውጦችና ባጋጠሙ ተግዳሮቶች ዙሪያ በቀረበ ሰነድ ላይ የጋራ የሆነ የውይይት መድረክ አካሂዷል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ አገራዊ ለውጡን ተከትሎ ባለፉት ሰባት የለውጥ ዓመታት በሀገራችን ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ እድገት ያስመዘገቡ ዘርፈ ብዙ ስራዎች በመሰራታቸው ግዙፍ ሊታይ የሚችል ውጤት በማስመዝገብ የዜጎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ መቻሉን አስገንዝበዋል፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ በመጣው ለውጥና በተገኘው መልካም እድል የተተገበረው የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ በኢኮኖሚው፣ በሰላም፣ በዲፕሎማሲና በሌሎች በርካታ ዘርፎችም ጭምር ከፍተኛ ውጤቶች ተመዝግበዋል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ሀገራችን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በመሸጋገር መሰረት ያለው ለሌሎች ሀገራት ተምሳሌት ሊሆን የሚችል እድገት ማስመዝገብ ተችሏል ብልዋል፡፡

በሀገራችን ይስተዋሉ የነበሩ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖሎቲካዊ ችግሮችን በመፍታትና አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት የተረጋጋ ሁሉን የሚያሳትፍ ስነምህዳር በመፍጠር ዜጎች ሀብት አፍርተው የሀገራዊ ብልፅግና ተሳታፊና ባለቤት እንዲሆኑ አስቻይ አውድ መፈጠሩን ገልፀዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ ሀገራዊ ለውጡ ተከትሎ ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስችላትን የዲጂታል ቴክኖሎጂ ምቹ ስነምህዳር በመገንባት ዘላቂና አካታች የዲጂታል ኢኮኖሚ ለማጎልበት በአይ ሲ ቲ መሰረት ልማት፣ በዲጂታል ክህሎት እና በህግ ማዕቀፍ ዝግጅት ረገድ የተሳካ ስራ በመሰራቱ የዲጂታል ኢኮኖሚውን እድገት ማረጋገጥ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

በዲጂታል ዘመን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችንና የፈጠራ አስተሳሰቦችን በማሳደግ ከኋላ ቀር አሰራር በመውጣት ለዜጎችን የህይወት መደላድልን በመፍጠር በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ የአሰራር ስርዓት እንዲፈጠር አስችሏል ብለዋል፡፡

መድረኩ በፓናል ውይይት የታጀበ ሲሆን ተሳታፊዎች ላነሷቸው ጥያቄዎች ከፍተኛ አመራሩ ምላሽ በመስጠት በቀጣይ ሊደመርና ፈጣን የኢኮኖሚ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል አቅም በመሰነቅ ሁሌም ያደገችና በአለም ተወዳዳሪ የሆነች ኢትዮጵያን ለመገንባት የድርሻውን መወጣት እንዳለበት በመድረኩ ተገልጿል፡፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ