+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ሀገራዊ ምርምሮች በተግባር ለማህበረሰቡ የእለት ተዕለት ህይወት መፍትሔ ሊሆኑ እንደሚገባ ተገለጸ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከአፍሪካ የቴክኖሎጂ ጥናት ማዕከል (ACTS) በተገኘ ድጋፍ ከተለያዩ የምርምር ተቋማትና ዩኒቨርስቲዎች ጋር በቅንጅት የሚያካሂዳቸውን ስድስት የምርምር ፕሮጄክቶች ያሉበትን ደረጃ ለመገምገም የሚያስችል መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ምርምር ለሀገር ልማት ቁልፍ መሣሪያ መሆኑን በማሳሰብ፣ ውጤታማ ምርምር ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።

ቀደም ሲል ውጤታቸው ወደ ተግባር የማይቀየር በሼልፍ ላይ ብቻ የሚቆይ ምርምር መኖሩን በማንሳት፣ አሁን ግን የዘመኑን ፍላጎት የሚመልሱ፣ በዕለት ተዕለት ህይወታችን ውስጥ መፍትሄ ማምጣት የሚችሉ የምርምር ውጤቶች እንዲመዘገቡ የሚያስችል አስቻይ ስነ-ምህዳር መገንባት እንደሚገባ አመልክተዋል።

በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ላይ የሚካሄዱ ምርምሮች የወጣቶችን ተሳትፎ በማጠናከር የስራ ዕድል ፈጠራን ማሳደግ እንዲችሉ እና በአጠቃላይ የሀገር አቀፍ ኢኮኖሚ ዕድገትን እንደሚያፋጥኑ አንስተዋል።

በሀገሪቱ ውስጥ የሚካሄዱ ብዙ የምርምር ስራዎች ውጤታማ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችና መፍትሄዎች ወደ ህብረተሰቡ እንዲደርሱ አልመው መስራት እንዳለባቸው ጠቁመዋል።

በመድረኩ ላይ የቀረቡት ምርምሮች በኢነርጂ፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በግብርናና በጤና ዘርፎች ላይ የተመሰረቱ ሲሆኑ፣ ከእነሱ መካከል አንዳንዶቹ ወደ ገበያ መግባታቸውና ለህብረተሰቡ ቀጥተኛ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸው ተገልጿል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ