+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ሀገራዊ የዲጂታል ኢኮኖሚ ስኬትን ለማረጋገጥ ጊዜውን የዋጀና የተሻሻለ የኢ-ሰርቪስ አገልግሎትን መጠቀም ግዴታ መሆኑን ዶ/ር ይሹሩን ዓለማየሁ ገለፁ

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ላይ ያለውን የኢ-ሰርቪስ አገልግሎት ዘመኑን የዋጀ እንዲሆንና ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ለመስጠት እንዲያመች በተሻሻለው ሲስተም ላይ ለዘርፉ ተዋናይ ማብራሪያ ተስጥቷል።

የዲጂታል ኢኮኖሚውን አቅም ለማጎልበት አገልግሎት እየሰጠ ያለውን ኢ-ሰርቪስ ጊዜውን የዋጀ፣ የዘመነና ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የያዘ እንዲሆን ለማሻሻል ያለመ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሹሩን ዓለማየሁ ሀገራችን በአለም ላይ እየዘመነና እየረቀቀ የመጣውን የቴክኖሎጂ እወቀት በመታጠቅ የዲጂታ ኢኮኖሚውን ለማጎልበት ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራች መሆኑን አስገንዝበዋል።

በኢትዮጵያ በተለያዩ ተቋማት ላይ አገልግሎት እየሰጠ ያለው ኢሰርቪስ በየጊዜው የሚሻሻል የአሰራር ስርዓቶች የሚያሳልጥ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በየጊዜው እየጨመረ የሚሂድ በመሆኑ በየተቋማት ያሉ በዘርፉ ላይ የተሰማሩ እና የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ላይ በትብብር ግንዛቤ መፍጠር እንደሚገባ ገልፀዋል።

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የብሔራዊ ኤሌትሮኒክስ መንግስት ልማት መሪ ስራ አሰፈፃሚ የተከበሩ ወ/ሮ ሚራጅ ዘክዬ አለምን ወደ አንድ አገልግሎት ያመጣው የዲጂታል አለም ይዟቸው የሚመጣቸውን መልካም እድሎቸ መጠቀም የሚያስችለንን የቴክኖሎጂ እውቀት በየጊዜው ልናሳድገው ይገባል ብለዋል።

አክለውም በሀገራችን አገልግሎት እሰጠ ያለውን የኢሰርቪስ አገልግሎት አዳዲስ ፊቸሮች ጨምረን ያሻሻልነው ሲሆን አገልግሎቱ እጅግ እንዲዘምን ስለሚያደርገው ሁሉም በትብብር ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ከተለያዩ ተቋማት በመውጣጣት የበውይይቱ ላይ የተገኙ የዘርፉ ተዋናዮች በቀረበው ማብራሪያ ላይ ላነሱት ጥያቄዎች መልስ ከመስጠትም አልፎ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በየተቋማቸው በመሄድ እገዛ እንደሚያደርግላቸው ተገልጿል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ