+251118132191
contact@mint.gov.et
ሀገር በቀል እውቀቶች ለሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ ሚና አላቸው፡፡ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጀ ሚኒስቴር ከተለያዩ የሀገራችን ክልሎች እና ተቋማት የተወጣጡ ከፍተኛ ሀላፊዎች ጋር በሀገር በቀል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዙሪያ የምክክር መድረክ አካሄዱ፡፡
በምክክር መድረኩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ አለም ፈጣን የሆነ የቴክኖሎጂ እድገት ማዘመንን በምታሳይበት ወቅት ያሉን ሀገር በቀል እውቀቶችን በማዘመን በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ የምናደርገውን ጉዞ ፈጣን መሆን አለበት ብለዋል።
የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲው ከተመላከቱት ዋና ዋና አላማዎች ውስጥ አንዱ የሀገር በቀል ዕውቀቶችን በማልማት ጥቅም ላይ ማዋል ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙት የሀገር በቀል ቴክኖሎጂዎችን በመለየት፣ በማዘመን እና በማበረታታት ቴክኖሎጂ የመጠቀምና የማምረት አቅማችንን ማሳደግ አለብን ብለዋል።
የጀመርነውን ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት በቴክኖሎጂ ለመደገፍ በማህበረሰባችን ውስጥ ያሉ ሀገር በቀል ቴክኖሎጂዎችን በምርምር በማገዝ፣ በመደገፍና ምቹ የሆነ ስነምህዳር በመፍጠር ወደ አምራችነት መቀየር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በምክክር መድረኩ የሀገር በቀል እውቅትን ለማልማት ባለድርሻ አካላት የሆኑት የየክልሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ተቋማት፣ የጤና ሚኒስቴር፣ የአዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን፣ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር፣ ምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን፣ ባዮና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እንዲሁም አርማወር ሃንሰን ምርምር ኢንስቲትዩት ተሳትፈዋል፡፡
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች