+251111265737

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ሀገር የሚፀናው ሁሌም በትውልድ መካከል በሚደረግ የመሰዋትነት፣ የልማት፣ የአንድነት ጉዞ ነው።ክቡር ዶ/ር በለጠ ሞላ

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር 17ኛው ሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ!” በሚል መሪ ቃል  አክብሯል፡፡

በዝግጅቱ ላይ የኢኖቬቨንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ለዚህ ሰንደቅ ዓላማ አባቶቻችን፣ አያቶቻችን፣ ዛሬም ድረስ ወንድምና እህቶቻችን ዋጋ የከፈሉበትና እየከፈሉበትም እንደሚገኙ አስገንዝበዋል፡፡

ሀገር የሚፀናው ሁሌም በትውልድ መካከል በሚደረግ የመሰዋትነት፣ የልማት፣ የአንድነት ጉዞ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ይህ ብዙ መሰዋትነት የተከፈለበት ሰንደቅ ዓላማ በዓለም መድረክ ስንቆም መለያችን፣ መታወቂያችንና ማንነታችን ስለሆነ ይህን ታሪካችንን አስከትለን ሀገራችንን በልማት የተሻለ እርምጃ እየተራመደች እንድትሄድ ሁላችንም ሀላፊነታችንን መወጣት አለብን ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ የብዙሃን ቋንቋ፣ ባህል፣ አመለካከት ባለቤት የሆነች ሀገር ነች ያሉት ክቡር ሚኒስትሩ እነዚህን ብዙሃነቶች በማስተናገድ ሀገራችንን የማሳደግ ሃላፊነት የዚህ ትውልድ በመሆኑ ጠንክረን መስራት ይኖርብናል ብለዋል።

የተቋሙ ሁሉም ሰራተኞች ኢትዮጵያውያን ድህነትን ኋላ ቀርነትን አስወግደው፣ ኢትዮጵያችንን በልማትና በዲሞክረሰሲ ጎዳና ውስጥ የህዝቦች ፍትሀዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ባጭር ጊዜ ውስጥ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራቶች ተርታ ትሰለፍ ዘንድ የጀመርነውን የለውጥ ጉዞ ወደ ማይቀለበስበት ደረጃ ለማድረስ በየጊዜው  እያጋጠሙን ያሉ ችግሮችን በማስወገድ በአንድነትና በጋራ ስሜት አብሮ በመቆም በአመቱ በመንግስት ትኩረት አግኝተው የታቀዱ ልማትና መልካም አስተዳደር ዕቅዶችን ለማሳካት፣ በሀገራችን ሰንደቅ አላማ ፊት ቃል ተገብቷል፡፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251111265737
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2026 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ