+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ሁለተኛው የኢትዮ-እስራኤል ኢኖቬሽን ሳምንት በተለያዩ ዝግጅቶች መካሄድ ጀመረ፡፡

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ መስክ በኢትዮጵያና እስራኤል መካከል ያለውን ፈጠራን እና ትብብር ለማጠናከር እንዲሁም የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ያለመው ይህ ዝግጅት ለአራት ቀናት የሚካሄድ ነው፡፡

ሁለተኛው የኢትዮ-እስራኤል ኢኖቬሽን ሳምንትን የከፈቱት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ የኢትዮጵያን የፈጠራ ገጽታ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር አለም አቀፍ ትብብር ያለው ጠቀሜታ የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።

"ኢትዮጵያ በአዲስ የፈጠራ ዘመን ገደል ላይ ትገኛለች"ያሉት ሚኒስትሩ ለዚህም ቴክኖሎጂን ለመቀበል የሚጓጓ ወጣት ፣ ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣ ስታርትአፕ እና አካባቢን ለማሳደግ ቁርጠኛ የሆነ መንግስት በቅንጅት ለፈጠራ አመች፣ ለለውጥ ዝግጁ ሁኔታ ላይ እንገኛለን ብለዋል።

እስራኤል በአስደናቂ የስታርትአፕ ባህሏ እና በቴክኖሎጂ እድገቷ ትታወቃለች ያሉት ሚኒስትሩ የእስራኤል የፈጠራ ሞዴል ለኢትዮጵያ ትምህርት ሰጭ በመሆኑ የትብብር ማዕቀፍ በመመሥረት በጋራ፣ ሃሳቦች የሚያብቡበት፣ ስታርትአፖች የሚበለፅጉበት፣ ቴክኖሎጂ ለኢኮኖሚ ልማት ማበረታቻ የሚሆንበትን ሁኔታ መፍጠር እንችላለን ብለዋል።

በዝግጅቱ ላይ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር የተከበሩ አቫራሃም ንጉሴ በዓለም ላይ ስኬታማና ግንባር ቀደም የፈጠራ እና ስታርትአፖ ሥነ-ምህዳርን በማቋቋም እንዲሁም በመንከባከብ ሀገራቸው ያላትን ልምድ በዚህ ፕሮግራም ለኢትዮጵያ የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚያጋሩ አንስተዋል።

ኢትዮጵያ በተፍጥሮ ሃብትና በሰው ሃይል የታደለች መሆኗን የገለጹት አምባሳደሩ ይህንን ሀብት በቴክኖሎጂ እና በኢኖቬሽን በመደገፍ ለኢኮኖሚ እድገት ለመጠቀም የሚደረገውን ጥረት ሀገራቸው እንደምታግዝም ተናግረዋል።

በዝግጅቱ ላይ በስታርትአፕ ስነ ምህዳር ግንባታ፣በኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ፣በታለንት ልማት እና ትምህርት፣በግንባታ ቴክኖሎጂና ሽግግር ላይ እስራኤል ያላት ተሞክሮ በሉእካን ቡድኑ ቀርቧል።

በኢትዮጵያ ያለውን የኢኖቬሽን ስነ-ምህዳር ለማሳደግ እየተሰሩ ያሉ የኢኖቬሽን ስትራቴጂክ ማዕቀፍ እና መሠረተ ልማት እንዲሁም አዳዲስ አሰራሮችን ለዘላቂ ልማት ለመጠቀም የተጀመሩ ስራዎች ለእስራኤል የሉዕካን ቡድን ቀርቧል፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ