+251118132191
contact@mint.gov.et
ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመራጭ የሴቶች ኮከስ አባላት በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ዋና ዋና ምሶሶዎችና አካታችነት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄ
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ የሥራ ስምሪትና የቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጋር በመተባበር ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመራጭ ሴቶች ኮከስ አባላት በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ዋና ዋና ምሶሶዎችና አካታችነት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል።
በመድረኩ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የምክር ቤቱ ምክትል አፈ-ጉባኤና የኮከሱ የበላይ ጠባቂ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ፤ ኢትዮጵያ ለጀመረችው ሁለንተናዊ ብልጽግና እና ለውጥ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ ሚና እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በልማትና በብልጽግና ጉዞዋ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንደምትገኝ የገለጹት የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ፤ የዲጂታል ቴክኖሎጂ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢኮኖሚ ዕድገትን እየመራ መሆኑን መንግሥት በመረዳት ለዘርፉ መጠናከር በትኩረት እየሠራ መሆኑን አንስተዋል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በበኩላቸው፤ የሀገሪቱን የዲጂታል ኢኮኖሚ በማጎልበትና አሠራሮችን በማዘመን የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት እንዲሁም የሚፈለገውን ለውጥና ዕድገት ለማምጣት የዲጂታል ዘርፉን በሚገባ ተገንዝቦ መጠቀምና ማስተዳደር ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" ያስገኛቸውን ሁለንተናዊ ውጤቶች በ"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ስትራቴጂ በማጠናከርና የታዩ ክፍተቶችን በመሙላት፣ ዓለም ከደረሰበት የኢኮኖሚ ዕድገት ጋር አብሮ ለመጓዝ የሚያስችል አቅም ለመፍጠር እየተሠራ መሆኑን ሚኒስትሩ አመላክተዋል።
የዲጂታል ስትራቴጂውን በተሻለ ሁኔታ ለመተግበር የሴቶች ተሳትፎ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሩ፤ ሴቶች በዘርፉ ያላቸው ሚና ስኬታማ ካልሆነ የተሟላ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብ አዳጋች እንደሚሆን አስገንዝበዋል።
የዲጂታል ዘርፉ የዜጎችን የሕይወት ዘይቤ መቀየር የሚያስችል መሆኑን በመጥቀስ፤ ማኅበረሰቡ የተሻለ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆንና በዲጂታል ቴክኖሎጂ ላይ በቂ አቅም እንዲፈጠር ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል።
የምክር ቤቱ አባላት በበኩላቸው ከመድረኩ ያገኙት ግንዛቤ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው፤ ዕውቀቱን እስከ ማኅበረሰቡ ድረስ ለማድረስ እንዲህ ያሉ የግንዛቤ መድረኮች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው በአጽንኦት ገልጸዋል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች