+251118132191
contact@mint.gov.et
ለስልጠና ዕድል ተጠቃሚዎች የወጣ ማስታወቂያ
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሀገራችንን የምርምር፣ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ልማት ስነ-ምህዳር ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመምራትና በመንግስት የተለዩ የልማት ግቦችን ለማሳካት ፖሊሲዎችን፣ ስትራቴጂዎችን፣ፕሮግራሞችን እና ፕሮጀክቶችን ቀርጾ በመስራት ላይ ይገኛል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ በ2014 ዓ.ም ተሻሽሎ በጸደቀው የሀገራዊ ሳይንስ፣ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ፖሊሲ ላይ ከተቀመጡ ቁልፍ የዘርፉ ልማት ሥራዎች ውስጥ አንዱ የሰው ሀይል ልማት በመሆኑ ሚ/ር መስሪያ ቤታችን በምርምር፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ልማት ሥራ የተሰማሩ ወጣት ተመራማሪዎችን እና የፈጠራ ባለሙያዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ online ስልጠና አመቻችቷል።
ስልጠናው ጥር 1 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ይጀምራል።
የዕድሉ ተጠቃሚዎች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ታህሳስ 26 / 2017ዓ.ም ከታች በተገለጸው አድራሻ (web link) በመጠቀም ማመልከት የምትችሉ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።
http://www.mint.gov.et/announcement-for-training...
ለበለጠ መረጃ +251 937904166 ላይ ይደውሉ።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች