+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ለኢትዮጵያ ዘላቂ ልማትና የቴክኖሎጂ ፈጠራ መሳለጥ የሜካኒካል ምህንድስና ማህበረሰብ ሚና የላቀ መሆኑን ዶ/ር ይሹሩን ዓለማየሁ ገለፁ።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ዘላቂና ጠንካራ ሀገራዊ የቴክኖሎጂ ልማት ለመገንባት የሜካኒካል ምህንድስና ማህበረሰብ ግንባታ ላይ አውደ ጥናት አካሄደ።

የሜካኒካል እና ኢንዱስትሪያል ምህንድስና ኮሌጅ በሜካኒካል ምህንድስና ዙሪያ የማህበረሰብ ግንዛቤ ለማስጨበጥ እና በዘርፉ ዓለም የደረሰበትን የቴክኖሎጂ አብዮት ለመፍጠርና ያለመ ነው።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ባዘጋጀው አውደ ጥናት ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሹሩን ዓለማየሁ በሀገራችን የቴክኖሎጂ ፈጠራን አቅም ለማጎልበት የሜካኒካል ምህንድስና እውቀትን መጠቀም እንደሚገባ ገልፀዋል።

ከቴክኖሎጂ ውጤቶች ጀርባ የሜካኒካል መህንድስና እውቀት እና ሙያ ከፍተኛ አበርክቶ አለው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ዓለማችን ወደ አምስተኛው የኢንዱስትሪ አብዮት እየተሸጋገረች ባለችበት ዘመን ሀገራችን በዘርፉ ተወዳዳሪና ተጠቃሚ ለመሆን የሚያስችላትን እድል ለመፍጠር በትብብርና በተናበበ አውድ መሰራት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም ምህንድስና የሰው ልጅን መሠረታዊ ፍላጎት ለማሟላትና የአኗኗር ስርዓት ለማሻሻል እንዲሁም ዘላቂ የልማት እድሎችን ለመፍጠር የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል።

አክለውም የሜካኒካል ምህንድስና ዘርፉን አቅም በማጎልበት ለሀገራዊ ሁለንተናዊ እድገት ልንጠቀምበት ይገባል ብለዋል።

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው አውደ ጥናቱ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የኢትዮጲያ ሜካኒካል ኢንጅነሮች ማህበር ተገኝተው ተሳትፈውበታል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ