+251118132191
contact@mint.gov.et
ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ስኬት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚና የላቀ እንደነበረ ተገለፀ።
የኢትዮጵያ “ዲጂታል 2025” ራዕይ ወደ ተግባር እንዲቀየር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በፖሊሲ፣ በቴክኖሎጂ መሠረት እና በዲጂታል ክህሎት ልማት ላይ ትኩረት በመስጠት የሀገሪቱን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን አንድ በመሪነት አፋጥኗል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በዲጂታል ስትራቴጂ አቅጣጫ ላይ የተወሰዱ እርምጃዎች የመንግሥትና የግል ዘርፍ አጋርነትን በማጠናከር የዲጂታል አገልግሎቶች በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲዘርጉ ዘርፈ ብዙ ስራዎች በመስራት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ ሚናውን ተወጥቷል ብለዋል።
ሚኒስቴሩ የኢ-መንግሥት አገልግሎቶችን በማስፋፋት የአገልግሎት ፍጥነትንና ግልፅነትን በማሳለጥ የሕዝብ እምነትን ከፍ አድርጎ የመንግሥት አገልግሎት ወጪን ለመቀነስ አስተዋጽኦ ማድረጉን አንስተዋል።
በቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት ዘርፍ የተደረጉ ስራዎች የኢንተርኔት ተደራሽነትን እና የዳታ አገልግሎት ጥራትን እንዲሻሻልና ለዲጂታል ኢኮኖሚ እንዲበቃ መሠረት መጣሉን ገልፀዋል።
የሰው ኃይል አቅም ማጎልበት በ“ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025” ስኬት ዋና መርሀ ግብር ስለነበረ ሚኒስቴሩ በስልጠና፣ በኮዲንግ እና በዲጂታል ችሎታ ፕሮግራሞች ወጣቶችን በስፋት እንዲሳተፉ ተደርጓል ብለዋል።
ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 የኢኖቬሽን ማዕከላትና የስታርትአፕ ፕሮግራሞችን በማጠናከር የአዳዲስ ሀሳቦች እድገት እንዲጎለብቱና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ወደ ገበያ እንዲገቡ አጋዥ የሚሆንበት ምቹ ስነምህዳር መፍጠር መቻሉን አውስተዋል።
ሚኒስቴሩ ከዓለም አቀፍ ተቋማትና አገሮች ጋር ትብብር በማጠናከር የቴክኖሎጂ ልምድ ልውውጥን እንዲሰፋና የአገር ውስጥ ችሎታን ለማሳደግ የሚያስችል ከፍተኛ ስራ መሰራቱን ጠቁመዋል።
“ዲጂታል 2025” በተግባር መሳካቱ በኢኮኖሚ፣ በትምህርት እና በአገልግሎት ዘርፎች አዎንታዊ ተፅዕኖ በመፍጠር የቴክኖሎጂ መፍትሄዎች እንዲፈጠሩ አስችሏል።
በአጠቃላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በመሪነት፣ በትብብርና በቀጣይነት ያከናወናቸው ስራዎች “ዲጂታል 2025” እንዲሳካ ዋና መሠረት በመሆን ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ትግበራ የላቀ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚቻል ማረጋገጫ የሰጠ ነው።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች