+251118132191
contact@mint.gov.et
መንግሥት በዕውቀት ላይ የተመሠረተ፤ በፈጠራ የሚመራ ኢኮኖሚ ሽግግር ለማፍጠን ባለፉት የለውጥ አመታት ለዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት እየሰራ ይገኛል፡፡የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ
በድሬዳዋ ከተማ አስተናጋጅነት በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና በኮርያ ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጄንሲ (KOICA) ትብብር ከሶማሌ፣ ከሀረሪ እና ከድሬዳዋ አስተዳደር ለአንድ ሳምንት በፈጠራ ሀሳብ ዙርያ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና እና ውድድር ተጠናቋል፤መድረኩ ወደ ቢዝነስ መቀየር የሚችል የፈጠራ ሀሳቦች የቀረቡበት ነበር።
በፕሮግራሙ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ወደ ቢዝነስ መቀየር የሚችል የፈጠራ ሀሳብ ያላቸው ወጣቶችን ስንደግፍ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን የዜጎችን ኑሮ በማሻሻል የኢኮኖሚ እድገት ውስጥ ከፍተኛ ሚና እንዳለው በማወቅ ነው ብለዋል።
በሀገር ደረጃ የምንገነባቸው የተለያዪ የኢንኩቤሽን ማእከላት መንግስት ለፈጠራ እና ለቴክኖሊጂ የሰጠውን ትኩረት ከፍተኛ መሆኑን የሚያሳይ ነው ያሉት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው መንግስት የስራ ፈጣሪ ወጣቶችን ፍላጎት ለማማሏት የተለያዩ ፖሊሲዎች እየተቀረፀ እንደሚገኝ አብራርቷል።
ሚኒስትር ድኤታው አዪይዘውም መንግሥት በዕውቀት ላይ የተመሠረተ፤ በፈጠራ የሚመራ ኢኮኖሚ ሽግግር ለማፍጠን ባለፉት የለውጥ አመታት ለዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
በኮርያ ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጄንሲ (KOICA) የፕሮጀክት አክሽን ኦፊሰር ኢንሱን ሚን ድርጅቱ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የኢንኩቤሽን ፕሮግራሞችን በመቅረፅ ፣ በኢንኩቤሽን ሴንተር መሰረት ልማት ግንባታ እንዲሁም ከ UNDP ጋር በመተባበር nin cradit fund ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ የሚገኝ መሆኑን በመግለፅ ቀጣይ በስታርትአፕ ዙሪያ መንግስት የሚሰራቸው ስራዎችም ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።
ከሦስቱም ክልሎች ለውድድር ከቀረቡት 115 ፕሮጀክቶች 15 ቱን ተለይተው ልዩ ስልጠና ሲሰጣቸው የቆዩ ሲሆን ከነዚም በ lemar learning, loca, ICT consultant services የቀረቡ ፕሮጀክቶች አሸናፊ ሆኗል።
ለአሸናፊ ፕሮጀክቶች በቅደም ተከተላቸው ከ250 ሺህ እስከ 100ሺህ የገንዘብ እና ቀጣይ በኢኖቤዝ ኬ ኢትዮጵያ ልዩ ክትትልና ድጋፍ ይደረግላቸዋል።
በዝግጅቱ ላይ የተገኙት የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጀዋር ከተማችን ወደ ስማርት ሲቲ ለመቀየር በምናደርገው ጥረት የፈጠራ ስራዎች ከፍተኛ ድጋፍ አላቸው ብለዋል።
ክቡር ከንቲባው ወጣቶች የፈጠራ ሀሳባቸውን የሚያሳድጉበትና የቴክኖሎጂ ተጠቃሚዎችና አምራቾች እንዲሆኑ ለማድረግ መንግስት ያመጣውን የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ተሳታፊ መሆን አላባችሁ የሚል ጥሪ አስተላልፈዋል።
በመድረኩም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ብቻ ሳይሆን ቴክኖሎጂ አምራች ወጣቶችን ለማፍራት የመጀረውን ድጋፍ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች