+251118132191
contact@mint.gov.et
መንግሥት የጀመራቸው የሠላም ውጥኖች እንዲሳኩ ሁሉም ሊያግዝ ይገባል-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
መንግሥት የጀመራቸው የሠላም ውጥኖች እንዲሳኩ ሁሉም ሊያግዝ ይገባል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብስባውን በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከምክር ቤቱ አባላት በተነሱላቸው ጥያቄዎች መነሻነት ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ እንዲሁም ቀጣናዊ፣አሕጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የዲፕሎማሲዊ ጉዳዮች ላይ ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ በፖለቲካዊ የሰላምና ደኅንነት ምላሽና ማብራሪያቸው ሰላም ለሰው ልጆች ለሁለንተናዊ እንቅስቃሴ መሰረት መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህ ሀገር ላይ የሚጨበጥ ለውጥ ለማምጣት የተሰነቀውን ህልም እውን ለማድረግ ሰላም በእጅጉ እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ሰላምን በተሟላ ሁኔታ ማረጋገጥ ካልተቻለ የሚታሰበውን ዕድገት ማስመዝገብ አስቸጋሪ እንደሚሆን አስገንዝበዋል።
በአማራም ሆነ በኦሮሚያ አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ጋር ንግግር መኖሩን ጠቅሰው፥ይህን አካሄድ የሚቃወሙ አካላት መኖራቸውን ጠቁመዋል።
ስለሆነም ተደጋጋሚ ግልጽ የሰላም ጥሪ መቅረቡን አስታውሰዋል።
በአገሪቱ በኋላ ታሪክም በኃይል ፍላጎትን ለማሳካት የሚደረገው አካሄድ ፍረጃና ጥላቻን በማስተጋባት ብዙ ጉዳት ማስከተሉን አንስተዋል።
በመሆኑም መንግሥት የጀመራቸው የሠላም ውጥኖች እንዲሳኩ ሁሉም ሊያግዝ ይገባል ነው ያሉት።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች